ይለፈኝ ባለማዕረጉ ይለፈኝ ባለጸጋው ይለፈኝ አጃቢ ያለዉ ይለፈኝ ባለጊዜው ይለፈኝ ያለኩት ወዳጄ ይለፈኝ የበላ ከእጄ ይለፈኝ ዘመዴ ያለኩት ገበናዬን ገልጬ ያሳየሁት አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፍኝ ይህቺ ቀን ፈቃድህ ሳይፈፀም አትለፍኝ ይህቺ ቀን ቃለህ ሳይበራልኝ አትለፍኝ ይህቺ ቀን የልብህን ሳትነግረኝ አትለፍኝይህቺ ቀን አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፍኝ ይህቺ ቀን ፈቃድህ ሳይፈፀም አትለፍኝ ይህቺ ቀን ቃለህ ሳይበራልኝ አትለፍኝ ይህቺ ቀን የልብህን ሳትነግረኝ አትለፍኝይህቺ ቀን በፍቅርህ የተገፉትን የምታቀርብ በትከሻህ የዛሉትን የምትሸከም በክንፎችህ ታናናሾችን ትይዛለህ በርህራሄ አይኖችህ የተጣለውን ታነሳዋለህ x2 ጣትህ ፈውስ ነው ህመም ለፀናበት ቃልህ ሠላም አለው ሃዘን ለገባው ቤት በብርና በወርቅ ሳይሆን አንተን ሰምቶ ስንቱ አረፈ በበዛው ሠላምህ እየተትረፈረፈ ጣትህ ፈውስ ነው ህመም ለፀናበት ቃልህ ሠላም አለው ሃዘን ለገባው ቤት በስጦታ ብዛት ሳይሆን አንተን ሰምቶ ስንቱ አረፈ በበዛው ሠላምህ እየተትረፈረፈ ይለፈኝ ሰው የጓጓለት ይለፈኝ የሚሯሯጥለት ይለፈኝ ከፍ ብሎ የታየው ይለፈኝ ለስጋ የሆነው ይለፈኝ የሚመስል ከፍታ የተናቀ በአንተ ዕይታ ነገር ግን ለአንተ ለሆነው ይኸው እጄን ከፍ አድርጌአለሁ አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፍኝ ይህቺ ቀን ፈቃድህ ሳይፈፀም ይህቺ ቀን ቃለህ ሳይበራልኝ ይህቺ ቀን የልብህን ሳትነግረኝ ይህቺ ቀን ለቁስል የሚሆን ዘይት በእጅህ አለ ያልጀመረ በእኔ ስንቱን ቤት ያከመ ዛሬም ከእኔ ደርሶ አይቀንስ ጉልበቱ ፈሶ ያድነኛል ያደርገኛል ብርቱ ለአንተ ብቻ እንድሆነ ካዛለኝ ሸሽቼ ሃሳቤን መንገዴን ሁሉዬን ሰጥቼ በደነገለ ሕይወት በማይሆን ለሌላ ሆኜ ልለቀልህ ፈጥነህ አግኘኝና አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፍኝ ይህቺ ቀን ፈቃድህ ሳይፈፀም ይህቺ ቀን ቃለህ ሳይበራልኝ ይህቺ ቀን የልብህን ሳትነግረኝ ይህቺ ቀን