ውሉን አልሳተም የህይወቴ ድውር ሥትክሰኝ አየው ስታሰማምር አንድ ብለህ እንደ ጀመርክ በክብር ስለ ምትቐጨው ዝም ቢዬ ልዘምር ይሁን አንተ እንዳልከው ውሉን አልሳተም የህይወቴ ድውር ሥትክሰኝ አየው ስታሰማምር ሀ ብለህ እንደ ጀመርክ በክብር ስለ ምትቐጨው ዝም ቢዬ ልዘምር ይሁን አንተ እንዳልከው አሜን 4* ያልከው ይሁን እሺ 3* በቃ ነፍሴ ትረፍልኝ ያለላትን አውቃ በወደድኩት ሳይፈስ ለኔ በተመቸኝ የህይወቴ ጎዳና ለምን ሲያሰኘኝ ሁሉን አያይዞ ለበጎ ሲያደርግ ባይኔ በብረቱ አየውት ሲለውጥ እርስትን ሲያድል ነጥቆ ከዚያ ሰነፍ ዘውትር ለሚተጋው ሊያልቀው ትላንት እንደ ሆነው ዛሬም እነደዛው ነው ስፍራን ላለቀቀ በቦታው ለቆየ አሜን 4* ያለው ይሁን እሺ 3* በቃ ነፍሴ ትረፍልኝ ያለላትን አውቃ የገዢ ቁጣ ሲነድ በላይ ፍንክች ላልል ላለቅ ስፍራዬን በትግስት ስፋት መቆየት ላደርግ ታላቁን ጥፋት ፀጥ እስክታደርግ ልኖር በቃልህ ልቤን አስፋልኝ ቀን እስኪመጣ እስክትፈርድልኝ ያደከመኝን እስክታደክመው የበቀል ጣትህን አይኔ እስኪያየው ድቅድቁን ስታዝ ላይቀር መንጋቱ ጎህ ሊቀድልኝ ሊያልፍ ለሊቱ የቀረ ይመስላል አንዲት እርምጃ ተራራው ሊናድ ሊሆን መሄጃ የወጀቡ አዛዥ የተራራው ሰሪ የሸለቆ ጌታ የጨለማው መሪ የማዕበሉ አዝማች የመብረቁ ንጉስ አንተ ነህ የኔ አባት የእስራኤል ቅዱስ 3*