Song Lyrics

እግዚአብሔር ፍቅር

Egziabher Fiker

Aster Abebe
Hallelujah
ጫካ አይወረድ እንጨትን ፍለጋ ቤትህን ለመስራት እንዲሆንህ ማረፊያ በወንድሞች ህብረት ፍቅር ትከብራለህ ሁለት ሦስት ስንሆን በዛ ትገኛለህ መጠበቅ ነው እንጂ ማጥበቅ ሰንሰለቱን ቀዳዳ አግኝቶ ክፉ እንዳይበትነን አንዱ ወንድም ሲደክም መቆም ሲያቅተው በፍቅር ደጋግፈን ምርኩዙ ከሆንነው የሚደፍረን ማን ነው መጠበቅ ነው እንጂ ማጥበቅ ሰንሰለቱን ቀዳዳ አግኝቶ ክፉ እንዳይበትነን አንዱ ወንድም ሲደክም መቆም ሲያቅተው በፍቅር ደጋግፈን ምርኩዙ ከሆነው የሚደፍረን ማን ነው ፍቅር ነው ፍቅር ነው እግዚአብሔር ፍቅር እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል እግዚአብሄር ፍቅር ፍቅር ነው ፍቅር ነው እግዚአብሔር ፍቅር እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል እግዚአብሄር ፍቅር ፍቅር ይታገሳል አንተ እንደታገስከን በሰፊው ትከሻህ እንደተሸከምከን ቅድስናችን ነህ ጽድቃችን ባንተ ነው በባዶ መኮፈስ መገበዙስ ለምን ነው? ፈቃዱን ለሳተ ከመንገዱ ወጥቶ ህመም ለጸናበት በጠላት ተመቶ አንገቱን ነቅንቆ የአንተ ፍቅር አያልፍም የወደቀን ማለፍ ባህሪይ አይደለም በዛ አትታወቅም ፈቃዱን ለሳተ ከመንገዱ ወጥቶ ህመም ለጸናበት በጠላት ተመቶ አንገቱን ነቅንቆ ያንተ ፍቅር አያልፍም የወደቀን ማለፍ ባህሪይ አይደለም በዛ አትታወቅም ፍቅር ነው ፍቅር ነው እግዚአብሔር ፍቅር እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል እግዚአብሄር ፍቅር ፍቅር ነው ፍቅር ነው እግዚአብሔር ፍቅር እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል እግዚአብሄር ፍቅር የአዳምን እርቃን ደርሶ ከሸፈነው የአባትነት ፍቅሩ አጋልጦ ካልሰጠው ይህ ህይወት በኛ አለ ከተጠቀምንበት ከራስ የሚያልፍ ፍቅር የተረፈ ህይወት ማገገሙ አይቀረም ምህረቱ አክሞት ወደ ጸጋው ዙፋን እንግፋው በጸሎት የሌላውን እርቃን ተባብረን ስንሸፍን ሞገስ አለ ከላይ የሚለቀቅልን በመያያዛችን ማገገሙ አይቀረም ምህረቱ አክሞት ወደ ጸጋው ዙፋን እንግፋው በጸሎት የሌላውን እርቃን ተባብረን ስንሸፍን ሞገስ አለ ከላይ የሚለቀቅልን በመያያዛችን ፍቅር ነው ፍቅር ነው እግዚአብሔር ፍቅር እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል እግዚአብሄር ፍቅር ፍቅር ነው ፍቅር ነው እግዚአብሔር ፍቅር እኛም ተጠርተናል እሱን እንድንመስል እግዚአብሄር ፍቅር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection