በሚናወጠው ላይ በጠነከረው ሰው ፈርቶ ዳር ቆሞ ለአይን ብቻ ባለው የፊት ጉዞዬን አይቶ ሊያጠነክረኝ በንፋሱ ግፊት ወደፊት ሊያፈጥነኝ በሚናወጠው ላይ በጠነከረው ሰው ፈርቶ ዳር ቆሞ ለአይን ብቻ ባለው የፊት ጉዞዬን አይቶ ሊያጠነክረኝ በንፋሱ ግፊት ወደፊት ሊያፈጥነኝ ለኔ በሚከብድ መንገድ በመሰለው ጉዜዬን ሲያደርገው ሞት ሞት በሚሸትት በመርከብ ስባሪ ነገዬን ሊቀጥለው አመንኩት ለነገ አብሮኝ ቆሞ ጎኔ እንዲያ ሲያበረታኝ ያለፈብኝ ወጀብ ጨመረልኝ ቁመት ወደሱ አስጠጋኝ አለሁ (3) በንፋሱ ብርታት ፍጥነት ጨምሬአለሁ አለሁ (3) በወጀቡ ጉልበት አቅጣጫን ይዣለሁ አለሁ (3) በማበሉ ብርታት ከዳር ደርሻለሁ አለሁ (3) ከፈተናው ብዛት ትእግስት ተምሬአለሁ በእኔም ቤት ገባ ቃልህ ፈቀድኩለት እንዲሰራ የፈራሰውን ነገሬን በውበቱ እንዲጠራ የቃልህ መንፈስ አግኝቶት ማን ቀጠለ እንደ ትናንት ደካማው ብርቱ ተባለ አልአዛር ወጣ በህይወት አለሁ (3) በንፋሱ ብርታት ፍጥነት ጨምሬአለሁ አለሁ (3) በወጀቡ ጉልበት አቅጣጫን ይዣለሁ አለሁ (3) በማበሉ ብርታት ከዳር ደርሻለሁ አለሁ (3) ከፈተናው ብዛት ትእግስት ተምሬአለሁ ጉዞ በባህር ላይ በማእበሉ ላይ አይኖቼን ተክዬ በአይኖቹ ላይ ጉዞ በበረሃ ጭው ባለው አይቀርም መድረሴ ተደግፌዋለው ጉዞ ከጌታ ጋር ከኢየሱስ ጋር ትናንት እንደረዳኝ ዛሬም ይረዳኛል ጉዞ በእቶን እሳት መሃል ጠፍቷል ወላፈኑ ወዳጄ ተገኝቶዋል