Song Lyrics

የልቤ አምላክ

Yelibe Amlak

Aster Abebe
Hallelujah
ዋላ ወደ ውሃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ ወደ አንተ ትገሰግሳለች ዋላ ወደውሃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ ወደ አንተ ትገሰግሳለች ቅርቤ ሆነህ ግን ነክቼ ያልጨረስኩህ የምትገባኝ ግን አውርቼ ያልቋጨሁህ የጨበጥኩህ ግን እሮጬ ያልደረስኩብህ የማወራህ ግን በቂ ቃል ያጣሁልህ እየበላሁህ የምትርበኝ እየጠጣሁህ የምትጠማኝ እየበላሁህ የምትርበኝ እየረካሁህ የምትጠማኝ ሁሌ እያየሁህ የምትናፍቀኝ ሁል ጊዜ አንተ ነህ የምታሰኘኝ አብሬህ እየዋልኩ የምትናፍቀኝ ሁል ጊዜ አንተ ነህ የምታሰኘኝ የተማርኩህ ግን እንዲህ ነህ የማልልህ ያስደነቅኸኝ ግን በቂ ቃል ያጣሁልህ የማብራራህ የቃል አቅም የሚያጥረኝ ያንተ ፍቅር እንዲህ ነው የሚያደርገኝ የልቤ አምላክ የምከተልህ እስካይህ ድረስ የምናፍቅህ የልቤ አምላክ የምከተልህ እስካይህ ድረስ የምናፍቅህ የበረሃ ጥሜን ያረካሁብህ አንተ የህይወት ውሃዬ ነህ የበረሃ ጥሜን ያረካሁብህ አንተ የህይወት ውሃዬ ነህ የምወድህ ውዴ የማፈቅርህ ፍቅሬ የምከተልህ እረኛዬ ምሰግድልህ አምላኬ አንተን ከአገኘሁ ሁሉን እረሳለሁ አንተን ከአገኘሁ ረክቼ አድራለሁ አንተን ከአገኘሁ ሁሉን እረሳለሁ አንተን ከአገኘሁ ረክቼ አድራለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection