ሚዛኑ ተዛብቷል ብዬ ላልኩት ጉዳይ አንተም ቸል ያልከኝ መስሎኝ የማልታይ ማጉረምረም ልጀምር ለምንን ላበዛ ላትጽናና ነፍሴ ለሊቱን በሙሉ እጆቼን ሳነሳ ላፍታ አንተን አሰብኩ ልቤን ደስደስ አለው ለቃልህ እንዲተጉ አይኖቼን ያዝካቸው ለሊት ነው ግን ከልቤ ጋራ ተጨዋወትኩኝ ነፍሴን በቃልህ አነቃቅተሃት ቆምኩኝ በረታሁኝ ላፍታ አንተን አሰብኩ ልቤን ደስደስ አለው ለቃልህ እንዲተጉ አይኖቼን ያዝካቸው ለሊት ነው ግን ከልቤ ጋራ ተጨዋወትኩኝ ነፍሴን በቃልህ አነቃቅተሃት ቆምኩኝ በረታሁኝ የተናገርከው ቃል አላለፈም ባህሪህ የሁሌ ነው አትጥልም አቅምን አገኘሁ ቃልክን ሳጠነጥን ስራህን ስጫወት ስናገር ምግባርህን ሰው መታመን ሳይችል ከስፍራው ቢታጣ አትልም የዛሬ አመት ላትደርስ ላትመጣ እምነቴ ተረድቶ በአንተ አቅም አግኝቼ ስንቴ ካልከኝ ደረስኩ እጆቼን ተይዤ እምነቴ ተረድቶ በአንተ አቅም አግኝቼ ስንቴ ካልከኝ ደረስኩ እጆቼን ተይዤ 1. ጆሮዬ ሰምቶ የነጻሁበት የሳተ ጎዳናዬን ያቀናሁበት የሚያምር ቃል ህይወት ማስዋቢያ እንደመስታወት ጉድፍን ማያ ነቅቼ ሰማሁ መልካም አገኘኝ አዕምሮዬን አድሶ ቀናውን አሳየኝ መልኩን መምሰያ አብ እንደሚወደው ድፍረቴ አይደል የአፍህ ቃል ነው የሚደንቅ ምክር (2) ስንቴ አመለጥኩበት ከጠላት ሽብር የሚደንቅ በረከት (2) ስንቱን የመከራ ዘመን አለፍኩበት የሚደንቅ ምክር (2) ስንቴ አመለጥኩበት ከጠላት ሽብር የሚደንቅ በረከት (2) ስንቱን የመከራ ዘመን አለፍኩበት 2.ለነፍሴ እስትንፋስ ለአጥንቴ ጤና የሚጣፍጥ ነገር እንደ ወለላ ለቆዳዬ ወዝ ዘይት የሆነ ድርቀቴን ገፎ እንዲህ ያስዋበ እድሜ ማርዘሚያ ቀን መጥገቢያዬ የነገዬ ሙላት መዳረሻዬ አቋራጭ አይደል መስራቴ ለፍቶ ቃልህ ይሞላዋል ቀድሞልኝ ወጥቶ 3. የቀኑን ክፋት ማሸንፍበት ትናንት ዘርቼ ዛሬ የማጭድበት መለምለሚያዬ እንደ ሰማይ ጠል አቅም ማግኛዬ እንድጠነክር የሚቆራርጥ በሁለቱም አፍ የተሳለ ነው ልክ እንደ ሰይፍ አጥንት ጅማቴን ዘልቆ የሚገባ የሚለውጠኝ ነው ነገዬን ማስዋቢያ የሚደንቅ ምክር (2) ስንቴ አመለጥኩበት ከጠላት ሽብር የሚደንቅ በረከት (2) ስንቱን የመከራ ዘመን አለፍኩበት የሚደንቅ ምክር (2) ስንቴ አመለጥኩበት ከጠላት ሽብር የሚደንቅ በረከት (2) ስንቱን የመከራ ዘመን አለፍኩበት