ለሁሉ ነፍስ ዘሪ ነህ ፍጥረት ያላንተ ባዶ ነው በአፍህ ቃል ጸንቶ ቆሟል ሁሉ አንድ ብሎ ቢራመድ በአንተ ነው ሁሉ ባዶ ጨለማ አንዳች በማይገኝበት ከሌለው ይህን ሁሉ ሞልተሃል አቤት ችሎታህ ያስብላል ሁሉ ባዶ ጨለማ አንዳች በማይገኝበት ከሌለው ይህን ሁሉ ፈጥረሃል አቤት ችሎታህ ያስብላል ቃላት የማይገልጽህ የማትብራራ የማትሰፈር የማትሰላ ልክህ ከቋንቋዎች ሰፈር የለ አንተ እራስህ አንተነህ ልክህ ከቁጥሮች መንደር የለ አንተ እራስህ አንተ ነህ ልክህ ከቋንቋዎች ሰፈር የለ አንተ እራስህ አንተነህ ልክህ ከቁጥሮች መንደር የለ አንተ እራስህ አንተ ነህ የሰማዩን ደመና በጥበብ ቆጥረሃል መብረቅ ሊታዘዝህ እነሆኝ ይልሃል የምድሩን ውሃ በእፍኝህ የቋጠርክ የምስራቁን ንፋስ በምድር ላይ የበተንክ ለማዕበሉ ትዕቢት ገደብ ይሁን ያልህ ሁሉን አሰልፈህ ስርአት ያስያዝህ በፍጥረትህ ታይተህ መደመም ሆነብኝ በማይነጥፍ አንደበት ማመስገን ይብዛልኝ በቃላት መደርደር በስንኝ ቋጠሮ ማን አክትሞ ያውቃል ስላንተ ዘርዝሮ ስራህ ለጠቢባን ሆናቸው መፍዘዣ አጥንተው እንዳያርፉ የእድሜ ልክ መጓዣ በጠብታ እውቀት ስንቱ አንጋጦ ቀረ ላይጨርስ ጀምሮ ዝንት አለም ቆፈረ ለኔ ግን በርቶልኝ የመስቀልህ እውነት ስራዬ አደረኩት ፍቅርህን መቀኘት አየሁ (4) በፍጥረቱ እግዚአብሄርን አየሁ አየሁ (4) በእጁ ስራ እግዚአብሄርን አየሁ አየሁ (4) ሰማዩን ሳይ እግዚአብሄርን አየሁ አየሁ (4) እራሴን ሳይ እግዚአብሄርን አየሁ ትልቅ ነው እግዚአብሔር ትልቅ ነው (2) ተምሬአለሁ እግዚአብሔር ትልቅ ነው (2) አይቻለሁ እግዚአብሔር ትልቅ ነው(2) አውቄአለሁ እግዚአብሔር ትልቅ ነው(2)