Song Lyrics

አንድ ቃል

And Kal

Aster Abebe
Hallelujah
ልንገርህ መውደዴን ለአንተ ያለኝን ከሰፈር ከሰው አሸፍቶ ጥፍት የሚያደርገኝን ልቤን ያጠፋውን ፋታ የማይሰጠኝን ሌላውን ለማሰብ ምክንያት እየሆነ በር የሚያዘጋኝን በሰበባ ሰበብ ፍቅር ነው የያዘኝ ፍቅር እንደ መልህቅ ሆኖ ከሌላው ያስጣለኝ ከአለም አጣልቶ ከአንተ ያጣበቀኝ ፍቅር የምሬን ነው የምወድህ ምርጫዬ አባቴ የኔ ፍቅር የምልህ ምቾቴን የሚያተወኝ ያለኝን የሚያስንቀኝ እጅ እጅህን ሳይሆን ፊትህን የሚያስናፍቀኝ ፍቅርህ ነው ፍቅር ነው የያዘኝ ፍቅር እንደ መልህቅ ሆኖ ከሌላው ያስጣለኝ ከአለም አጣልቶ ከአንተ ያጣበቀኝ ፍቅር ለውድድር የማይቀርብ የበረታ ፍቅር በልጠህ የምትናፍቀኝ በተጠጋሁህ ቁጥር ከፍዬ የማልሰጠው ለሌላው ቆርሼ ልቤ እኮ የአንተ ነው የፍቅር ምላሼ ከፍዬ የማልሰጠው ለሌላው ቆርሼ ልቤ እኮ የአንተ ነው የፍቅር ምላሼ ምን ብል አያረካኝ ደርሶም አያጠግበኝ ሁሉ የተራቆተ የሚያስንስህ ሆነብኝ አንድ ቃል አገኘሁ የምደጋግመው ልቤ ላይ ጠብ ያለ ነጋ ጠባ የምለው እንካ ይኸው እገሰግስሃለሁ አንድ ቃል አገኘሁ የምደጋግመው ልቤ ላይ ጠብ ያለ ነጋ ጠባ የምለው እድሜ ልኬን እኔ እፈልግሃለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection