ሐሳብህ ጥልቅ ዕቅድህ የተለቀ ከሰፈሬ ርቆ ከሰማይ የላቀ ይሁን ያልከው ብዬ በዚያ ደምድሜአለሁ በጎ ስለሆነ ለኔ የምታስበው ከአንተ ተከራክሮ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ የቻለ ሊያወራ ጀምሮ አንገቱን ቀና አድርጎ ቆሞ የቀጠለ ሊያርምህ የዳዳው ሊያስተካክልህ እኮ የቱ አዋቂ ነው ተው በዚህ ነው የሚልህ በዝቶ ካለው ጩኸት ሸተተኝ ሰላሙ ከጨለማው መሃል ታየኝ ወጋገኑ ከድፍርሱ መሃል ኩልል ያለ ነገር ይታየኝ ጀመረ በቃልህ ስታመን የሃሳብህ ጥልቀት ባይገባኝ ድምድሙ ጅማሬ ላይ ቆሜ ቢበዛ ለምኑ የፍርስራሽ ክምር ግራ ቢያሳስበኝ ማዶን አሻግሬ ለማየት ሲያቅተኝ ጎራ ስል ወደ ቃልህ ነገረኝ ነገሩን የዛሬው ትርምስ ነገ ላይ ማማሩን ለአይን የሚመች ነገር ባያዩም አይኖቼ ግን በስራ ላይ ነህ ልቀመጥ ረግቼ (2) የለም ከሰው ሰፈር የፈቃድህ ምክር ፍጥረትን ሰብስበህ አትቆም ለድርድር ለዝብርቅርቁ ቅርጽ መልክ ላጣው ውበት ሰተት ብሎ ይገባል አሜን ባለ አንደበት ዝምታህ መልስ ሆነኝ አሃ አሃ ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2) እየሰራህ እንዳለህ ጨለማው ነገረኝ ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2) በስራ ላይ እንዳለህ ድፍርሱ ነገረኝ ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2) ዝምታህ መልስ ሆነኝ አሃ አሃ ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2) ለዚህ ነው ባትለኝ ድፍርሱ ነገረኝ ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2) በስራ ላይ እንዳለህ ሁኔታው ነገረኝ ዝምታህ መልስ ሆነኝ (2)