ከምርኩዜም አያልፍ ማይዘል ከማገጃ በእጄ የከረመ ድጋፍ መወጣጫ ያን ዕለት ገብቶኛል ትኩረቴን ስትስበው በሚነድ ቁጥቋጦ እግሬን ስታፈጥነው የሰጠኸኝን መልሼ ብጥል ከእግሮችህ ስር እንደ ምትሰራበት ባንተው እጅ እንዲያምር አውቂያለሁ እንካ ጊዜዬን ተጠቀምበት በልብህ እንዳለው አከናውንበት እንካ ያለኝን ወርቅና ብር እኔ ጋር ሆኖ ጓዳ እንዳይቀር ምን ክፋት አለው ቢያገለግለኝ ሀገር ሁሉ ያውቃል እንደሰጠኸኝ እንደተቀበልኩት በለቅሶ በእንባ በስለት ክምር ቤቴ እንደገባ ከሚሆን የራሴ እኔ ጋር ቀርቶ መልሼ ልስጥህ የሌላውን በልጦ ስስት ሳይዘኝ አንዴ ሳልልህ ይኸው አኖርኩት ከእግሮችህ ስር አሜን ይሁና ሳሙኤልን እንካ ትርፍም ባይኖረኝ እሱን ሚተካ ይለፍ ካንቺ ካልክ ካልክ አምጭው ለኔ ለትውልድ ይሁን ይለፈኝ እኔ ሽታውን ሳልጠግበው የልጅነቱን መልሼ ሳላይ ጨዋታ ሳቁን ጥቂት ቆይቶ ሳያባብለኝ እንካ በማለዳ ተቀበለኝ እንካ ጊዜዬን ተጠቀምበት በልብህ እንዳለው አከናውንበት እንካ ያለኝን ወርቅና ብር እኔ ጋር ሆኖ ጓዳ እንዳይቀር ሁለት አሳና አምስት እንጀራ ከኔ አያልፍም በሰው ሲሰላ ለራሴ ነበር ፈልጌ የያዝኩት ራቡ ሲጠና ልጎርሰው ያልኩት ያንተ ግምት ከልክ አለፈ ብዙ ልታጠግብ ከአጄ ወስደህ አንቢ አልልም ስስት ለቆኛል ከንግዲህ ወዲያ እልፍን ይሸኛል አስደምሞኛል ተደንቄያለው ጥቂት ነበረ በእጄ ላይ ሳየው ይለፍ ካንቺ ካልክ ሀገር ሊያበላ ይውጣልኝ ከእጄ ይሁን ለሌላ እንካ ጊዜዬን ተጠቀምበት በልብህ እንዳለው አከናውንበት እንካ ያለኝን ወርቅና ብር እኔ ጋር ሆኖ ጓዳ እንዳይቀር