Song Lyrics

ከሙሴ የሚልቅ

Kemuse Yemilike

Aster Abebe
Hallelujah
በአመፅ ተፀንሶ ኃጢአት ሆና እናቱ ሞት ለሆነ አለሙ ሲኦል መደምደሚያው እንዲሆን ለታጨ ታይቶህ መባዘኑ ሩቅ ለነበረ ህዝብ ወደ ግዛትህ መጥሪያ አቁመህ ምልክት ከምድር ዳርቻ ጠራህ በፉጨትህ ያላወቀህን ትውልድ እየተጣደፍን በፍጥነት መጥተናል ድካም ድንዛዜን ፍርሃት ጨለማን ከኛ ላይ ሰብረሃል የተናቅነውን ምርጥ የተጣልነውን ቅዱስ ልትለን ያላፈርህ የጸጋ ሁሉ አምላክ የሆንህ እግዚአብሄር ክቡር ስምህ ይባረክ ምህረት ለወደደ ለሮጠም አይደለ መማርን በምታውቅ በአንተ ለኛ ሆነ ለፍቅርህ ማሳያ ህዝብ ብለህ መረጥከን ለጥፋት ለሆንን የቁጣ እቃዎች ትዕግስትህ ቻለን የህግ መሰጠት የመቅደስ ስርዓት ኪዳን ላልነበረን ውብ የተስፋ ቃላት የጥሉ ግድግዳ ከማዶ ላረገን ዕውር ለስርአትህ አህዛብ ለተባልን ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ የህልውናህን ስፍራ እንዳያይ አይናችን ሆኖን መጋረጃ ከልሎ ሃጥያታችን ይዞን እንዲገባ ከማዶ እንዳንቀር ስለ እኛ ቀደመ ገባ በመካከል ተልኮልን ለነፍሳችን መልህቅ ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ የእንቅፋት ድንጋይ ማሰናከያ አለት አኑሮ በጽዮን አምነው እንዲድኑበት በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን ቅን ፈቃዱ ሆና ጥንት ተወስኖልን ተልኮልን ለነፍሳችን መልህቅ ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ ተልኮልን ለነፍሳችን መልህቅ ሊቀ ካህን ከአሮን የሚልቅ ላክልን ለነፍሳችን መልህቅ ሊቀ ካህን ከሙሴ የሚልቅ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection