Song Lyrics

ወደ ተራራው ጫፍ

Wede Teraraw Chaf

Aster Abebe
Hallelujah
ከህልውናህ ሰፈር ከምትገኝበት ንግግር ጸሎቴ አንተው ከሆንክበት ጠንቀቅ ካላልኩኝ ካልጠበቅኩ እግሮቼን እልፍ የሚለይ ጉዳይ ከቦኛል ዙሪያዬን በገለባ ናፍቆት በጠፊ ፍለጋ አይለፍብኝ ቀኔ አርቆኝ ከአንተጋ ወደ ተራራው ጫፍ ሳበኝ ወደራስህ ነፍሴም ድና እንድትቀር አቅልጣት በክብርህ በገለባ ናፍቆት በጠፊ ፍለጋ አይለቅብኝ ቀኔ አርቆኝ ከአንተጋ ወደ ተራራው ጫፍ ሳበኝ ወደራስህ ነፍሴም ድና እንድትቀር አቅልጣት በክብርህ መባዘን አይደለም መዋል ከአንተ ጋራ ስለ ላዩ ምክርህ ነፍሴን ስታዋራ ሰብሰብ ብሎዋል ቀኔ አልተዝረከረከም የማይወሰድ ዕድል ከዚህ በላይ የለም መባዘን አይደለም መዋል ከአንተ ጋራ ስለ ላዩ ምክርህ ነፍሴን ስታዋራ ሰብሰብ ብሎዋል ቀኔ አልተዝረከረከም የማይወሰድ እድል ከዚህ በላይ የለም አንተን ብቻ ይሁን የማይበት አይኔ ልቤ ሄዶ ይቅር ከላዩ ሰፈሬ ጆሮዬም ይቀሰር ከላይኛው ሃገር አጥፋኝ ከምድሩ ፍለጋዬ ይሰወር አንገቴን አስግጌ በመናፈቅ ህይወት ለአፍታ ጎንበስ ሳልል አንዳች ከሌለበት እጅ ሰጥቶ ለአንተ ውስጥና ውጪዬ ስንቄ ሆኖ ፍቅርህ ይጠቅለል እድሜዬ አንገቴን አስግጌ በመናፈቅ ህይወት ለአፍታ ጎንበስ ሳልል አንዳች ከሌለበት እጅ ሰጥቶ ለአንተ ውስጥና ውጪዬ ስንቄ ሆኖ ፍቅርህ ይጠቅለል ዕድሜዬ ጥሜ ረሃቤ ናፍቆቴ መሻቴ ጉጉቴ ፍላጎቴ ሩጫዬ መገስገሴ አንተን ለማግኘት ነው ጥሜ ረሃቤ ናፍቆቴ መሻቴ ጉጉቴ ፍላጎቴ ሩጫዬ መገስገሴ አንተን ለማግኘት ነው በቃ እፈልግሃለሁ በቃ ተርቤሃለሁ በቃ በጣም ጠምተኸኛል በቃ አይኖቼ ናፍቀውሃል በቃ ናፍቄሃለሁ በቃ ደጅ ደጅ አያለሁ በቃ የውስጤ ጥም ነህ በምንም የማልለውጥህ አንተን የተራበ የሚጠግበው አንተን ነው አንተን የተጠማ የሚረካው አንተን ነው ፊትህን የፈለገ ሲያገኝህ ያርፋል ፈልጎ ክብርህን በእጅህ መች ይረካል አይደለሁም ሰነፍ ተመከርኩ በቃልህ የውስጤን ረሃብ አይደፍነውም የእጅህ ነፍሴን የምታረካ ሙላት ነህ የልቤ የኑሮዬ ፍሰሃ የዕድሜ ልክ ሃሳቤ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection