Song Lyrics

ብዛልኝ

Bizalign

Aster Abebe
Hallelujah
አንተ የሌለህበት ቦታ ለምኔ ሃገር ለምኔ ከፍታ ለምኔ አንተ የሌለህበት ህብረት ለምኔ መዝሙር ለምኔ ወሬ ለምኔ አንተ የሌለህበት ቦታ ለምኔ ሃገር ለምኔ ከፍታ ለምኔ አንተ የሌለህበት ህብረት ለምኔ መዝሙር ለምኔ ወሬ ለምኔ አስጠጋኝ ወደ ዕቅድህ ወዳየህልኝ ወደ ሃሳብህ ኧረ አስጠጋኝ ወደ እቅድህ ወዳየህልኝ ወደሃሳብህ የእግሮቼን ጉዞ መትርልኝ የአንደበቴን ቃል ስፈርልኝ ለፈቃዴ ገደብን አብጅለት ሞገደኛው ልቤ ይወቅ ለከት አስተምረኝ ምን ትላለህ ማለት የእግሮቼን ጉዞ መትርልኝ የአንደበቴን ቃል ስፈርልኝ ለፈቃዴ ገደብን አብጅለት ሞገደኛው ልቤ ይወቅ ለከት አስተምረኝ ምን ትላለህ ማለት አይኖቼ እያዩ ቅጥቅጧን ሸንበቆ ደግፈህ ስታቆመኝ እያወቀ ልቤ የምጤሰውን ጧፍ ቀርበህ ስታበራኝ ጆሮዬ እየሰማ ለራስ የማልበቃውን ስታተርፈኝ ለሃገር በቀረልኝ እድሜ ከአንተ ሌላ ውጪ አፌ ምን ይናገር አሁንም ብዛልኝ እንዲረዝም እድሜዬ አብልጬ ልጠጋህ እንዲደምቅ ማታዬ ሁነኝ መዋያዬ በቀረልኝ ዘመን መንገዴ እየነጋ እስኪሆን ሙሉ ቀን አሁንም ብዛልኝ እንዲረዝም እድሜዬ አብልጬ ልጠጋህ እንዲደምቅ ማታዬ ሁነኝ መዋያዬ በቀረልኝ ዘመን መንገዴ እየነጋ እስኪሆን ሙሉ ቀን ውሎ ከአንተ ጋራ አድሮና ሰንብቶ ማን በትናንት ቀረ ከአንተ ብዙ ቀድቶ የለውጥ ጅማሬ ነህ የህይወት ማጣፈጫ የተጠጉህ ሁሉ ወጥተዋል በብልጫ ውሎ ከአንተ ጋራ አድሮና ሰንብቶ ማን በትናንት ቀረ ከአንተ ብዙ ቀድቶ የለውጥ ጅማሬ ነህ የህይወት ማጣፈጫ የተጠጉህ ሁሉ ወጥተዋል በብልጫ ሰሞነኛ እንዳልሆን አድሮ እንዳልሰለች ጉልበቴን ላስጠጋ ወደ ቃሎችህ ደጅ ዘመንን ዘላቂ እንዲሆን ነገሬ ዙረቴን አቁሜ ልፈልግህ ዛሬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection