እረሳሁት ጥያቄዬን የከበበኝን በዙሪያዬ ስቀርብ ፊትህ ለማመስገን ቀሎ ታየኝ ሁሉም ነገር (2) ሳላመልክህ ጊዜው አይለፍ የሚገባህን ምስጋና ሳላቀርብ ሞልቶ ላይሞላ የምድሩ ነገር ካልክልኝ አልጎድልም ለጭንቅ ውሎ ማደር ርቋል ከኔ ሰፈር (2) አመልክሃለው (3) በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ አመልክሃለው (3) በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ ለተራራው ቁመት እያልኩኝ ትልቅ ነህ ለሸለቆው ጥልቀት እያልኩኝ ሙላት ነህ ለሞገዱ ብርታት እያልኩኝ ሰላም ነህ ለጨለማው ርዝመት እያልኩኝ ብርሃን ነህ አመልክሃለው (3) በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ ብዙ ጊዜ ታገልኩ ከቃላቶች ጋራ ስላንተ ማንነት በዝርዝር ላወራ አንሰው ተገኙብኝ ያለኝ ሁሉ አላረካኝ እንደገባኝ መጠን እንኳን ልገልጽህ አቃተኝ (2) ማንም እንደሚልህ አይደለህም ከመታወቅ ታልፋለህ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ (2) (ትልቅ ነህ)x2 እግዚአብሔር ትልቅ ነህ (4) ካነበብኩት አይደል ከሰው የሰማሁት ዛሬ በዚህ ሰዓት ፊትህ ያመጣሁት ከነፍሴ ምስጋና ከውስጠቷ የሆነ አፌን ሞልቶ የሚፈስ አዲስ ቅኔ አለ (2) ያላነሰ ያላጠረ ከላይ ከላይ ያልሆነ ለእኔ ፍቅር ለኢየሱሴ አለኝ ምስጋና ከነፍሴ (2) አለኝ ምስጋና!