Song Lyrics

ፍለጋው አደረገኝ

Filegaw Aderegegn

Aster Abebe
Hallelujah
እንደገናን ባያውቅ ዳግም ዕድል ባይሰጥ ማን ይችል ነበረ የጌታ ደጅ ሊረግጥ እየተደገፈ በማይሰፈር ፀጋው እንደኔ የቆመ ስንቱን ቤት ይቁጠረው ስንቱን ቤት ይቁጠረው እንደገናን ባያውቅ ዳግም ዕድል ባይሰጥ ማን ይችል ነበረ የጌታ ደጅ ሊረግጥ እየተደገፈ በማይሰፈር ፀጋው እንደኔ የቆመ ስንቱን ቤት ይቁጠረው ስንቱን ቤት ይቁጠረው ደጋግሞ የተፈተነ እምነቴ እንዳይንኮታኮት አልቆለት እንዳይወድቅ እንደስንዴ ሊያበጥረኝ የወጣውን ፈታኝ በ ‘አይቻልም’ ሲሰድ የአንደበቴን ሳይሆን ያወቀ የልቤን እንደተመኘሁት ልሆን ያለመቻሌን እስኪቆሙ እግሮቼ በብዙ አገዘኝ ሃይልን እስክቀበል አይዞሽ በርቺ እያለኝ ያለቀልኝ መስሎት ለሳቀብኝ ጠላት ማልዶ ማለደልኝ ጉልበቴን አጸናት ያለቀልኝ መስሎት ለሳቀብኝ ጠላት ማልዶ ማለደልኝ ጉልበቴን አጸናት ክህደት መሃላዬን አላውቀውም ማለቴን ዶሮ ሶስቴ እስኪጮህ አልፎ መጨመሬን ከትንሳኤው ማግስት ብርቱዎች እያሉ ከሰነፎች ተርታ እንደኔ ያልዋሉ ፍልጋው አረገኝ መጣ ወዳለሁበት ሊቀጥለኝ ዳግም ከተቆረጥኩበት ፍለጋው አደረገኝ መጣ ወዳለሁበት ሊቀጥለኝ ዳግም ከተቆረጥኩበት ፍለጋው አደረገኝ መጣ ወዳለሁበት ሊቀጥለኝ ዳግም ከተቆረጥኩበት ፍለጋው አደረገኝ መጣ ወዳለሁበት ሊቀጥለኝ ዳግም ከተቆረጥኩበት በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው በማለዳ ምስጋናዬ ይኸው በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው ለተቤዠኝ ምስጋናዬ ይኸው በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው ሳላቋርጥ ምስጋናዬ ይኸው በትንሽ አዕምሮዬ ስላሰብኩት ነገር ብዕሬን ይዣለው ቃላትን ቀምሬ በዜማ ልናገር አልችልም ልደብቅ የውስጥ ደስታዬን እሱ በኔ ሆኖ ነውሬን አስወግዶ ከሰው መቆጠሬን ዝም ይባላል እንዴ ደግሞስ ያስችላል ወይ አትረፍርፎ አድርጎልኝ ረድኤቱን ከላይ የቃላትን ድንበር ጥሶ ያለፈ መውደድ አንድ ልጁን ሰጥቶ የራሱ የሚያደርግ አጽናንቶኛል ባድማ ህይወቴን በመልካምነቱ ሞልቶ አስደሰተኝ በረሃ ህይወቴን እንደ ኤደን አድርጎ ተድላ አደለኝ የደስታ የቅኔ ድምጽ ወጣ ከቤቴ መራቄ ቀርቶ ቀርቤአለሁ አብ ሆኖኝ አባቴ አጽናንቶኛል ባድማ ህይወቴን በመልካምነቱ ሞልቶ አስደሰተኝ በረሃ ህይወቴን እንደ ኤደን አድርጎ ተድላ አደለኝ የደስታ የቅኔ ድምጽ ወጣ ከቤቴ መራቄ ቀርቶ ቀርቤአለሁ አብ ሆኖኝ አባቴ በትንሽ አዕምሮዬ ስላሰብኩት ነገር ብዕሬን ይዣለው ቃላትን ቀምሬ በዜማ ልናገር አልችልም ልደብቅ የውስጥ ደስታዬን እርሱ በኔ ሆኖ ነውሬን አስወግዶ ከሰው መቆጠሬን ዝም ይባላል እንዴ ደግሞስ ያስችላል ወይ አትረፍርፎ አድርጎልኝ ረድኤቱን ከላይ የቃላትን ድንበር ጥሶ ያለፈ መውደድ አንድ ልጁን ሰጥቶ የራሱ የሚያደርግ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection