Song Lyrics

በቃኝ የማልለው

Bekagn Yemalilew

Aster Abebe
Hallelujah
እንደገና ረሃብ እንደገና ጥማት ትናንት ምንም እንዳላየ እንደገና ናፍቆት እንደገና ጉጉት አንተ ወዳለህበት እንደገና ረሃብ እንደገና ጥማት ትናንት ምንም እንዳላየ እንደገና ናፍቆት እንደገና ጉጉት አንተ ወዳለህበት ጥቂት አንተን ቀምሶ እንደ ጠገበ ሰው መሆን የጤና አይደለም ረሃቤን ፈውሰው ጥቂት አንተን ቀምሶ እንደ ጠገበ ሰው መሆን የጤና አይደለም ረሃቤን ፈውሰው እለት እለት ባዶ ትሁን እና ነፍሴ በመገኘትህ ውስጥ ይረስርስ መንፈሴ እለት እለት ባዶ ትሁን እና ነፍሴ በመገኘትህ ውስጥ ይረስርስ መንፈሴ በቃኝ የማልለው ይለፈኝ የማልለው ሰለቸኝ የማልለው ያንተ ህልውናህ ደስታዬ ያለበት ያለፈ ሰላሜ መገኘትህ ነው መዋያ ማደሪያዬ ናና እስኪ አጠጣኝ ናና እስኪ አጉርሰኝ የእጅህን ሳይሆን ክብር መልክህን የምድሩን ሳይሆን ህልውናህን ሌላውን ሳይሆን አንተው እራስህን ናና እስኪ አጠጣኝ ናና እስኪ አጉርሰኝ የእጅህን ሳይሆን ክብር መልክህን የምድሩን ሳይሆን በላይ ያለውን ሌላውን ሳይሆን አንተው እራስህን የፊትህን ሳይሆን ፈልጎ የእጅህን ባትገባም ከቤቴ ላክ ብቻ ቃልህን የእምነቱን ቁመት አድንቀህ እንዳለፍከው አንተን በደጅ ትቶ ፈውሱን ብቻ እንዳለው አይደል መገስገሴ ፊትህን ማለቴ ማድጋዬን ልሞላ ላሰማምር ቤቴን ይሁን ሁሉ እንዳለ ከነ ዝብርቅርቁ ከአንተ ካልከተመኝ ካቆመኝ በሩቁ ሳበኝ በእጆችህ ወደ ክብርህ ጥልቅ አስገባኝ ከእልፍኝህ ጅምሩም ባያልቅ በቃኝ የማልለው ይለፈኝ የማልለው ሰለቸኝ የማልለው ያንተ ህልውናህ ደስታዬ ያለበት ያለፈ ሰላሜ መገኘትህ ነው መዋያ ማደሪያዬ በቃኝ የማልለው ይለፈኝ የማልለው ሰለቸኝ የማልለው ያንተ ህልውናህ ደስታዬ ያለበት ያለፈ ሰላሜ መገኘትህ ነው መዋያ ማደሪያዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection