Song Lyrics

ሃሌሉያ

Hallelujah

Aster Abebe
Hallelujah
በሰላሙ ብዛት ቀለለ ችግሩ አደገ ቁመቴ እያለ ነገሩ ቀረ መዋከቤ በጠራኸኝ ሳርፍ ተምራልኝ ነፍሴ አንተ ላይ ማራገፍ ድምጿ ተቀየረ ተለወጠ ቃሏ እዬዬን በእሰየው የአንተ በመሆኗ እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን ለለወጥከው ኢየሱስ እንካ ዘላለሜን ድምጿ ተቀየረ ተለወጠ ቃሏ እዬዬን በእሰየው ያንተ በመሆኗ እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን ለቀየርከው ኢየሱስ እንካ ዘላለሜን ተባረክ እልሃለሁኝ (8) ተንበርክኬ አሸነፍኩኝ እጅ ሰጥቼ ድል ነሳሁኝ በጩኸቴ መዳን ሆነ አበሳዬ ተከደነ ተከትዬህ ከፊት ቀደምኩ ያንተን ብዬ ከምን ጎደልኩ ስፈልግህ ጸኑ እግሮቼ ሃይሌ ሆነኸኝ ተሟጋቼ በመጨነቅ ስርአትህን በመማጸን መጓደድን በር በመዝጋት ክፉን ማምለጥ እርዳኝ ብዬ ሁሉን መብለጥ ከአንተ ሰምቶ የውስጥ ውበት አቤት ብዬህ አለኝ ማለት ከአንተ ዘግኖ ሞልቶ ማደር ሆኖልኛል ስምህ ይክበር ስኬቴ በአንተ መታመኔ ከፍታዬ እግርህ ስር መሆኔ ውበቴ አንተን መጠጋቴ ድምቀቴ ምህረትህ ነው ለኔ ስኬቴ በአንተ መታመኔ ከፍታዬ እግርህ ስር መሆኔ ውበቴ አንተን መጠጋቴ ድምቀቴ ምህረትህ ነው ለኔ አሃ ሃሌሉያ (4) እላለው ሃሌሉያ አሃ ሃሌሉያ (4) እላለው ሃሌሉያ በማለዳ ሃሌሉያ በቀትር ሃሌሉያ በምሽት ሃሌሉያ በሌሊት ሃሌሉያ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ሃሌሉያ ሳይቀየር ሃሌሉያ እላለው ሃሌሉያ አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ አሃ ሃ ሃ ያሌሉያ ኦሆ ኦሆ ኦሆ ሃሌሉያ አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ ኦሆ ኦሆ ሃሌሉያ አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ ኦሆ ኦሆ ኦሆ ሃሌሉያ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection