ለሚያወራህ ውበት ለሚለብስህ ጌጥ ሮጦ ለተጠጋህ የማምለጫ አለት ህይወት ከሞት ወዲያ እርስቱ ላረገህ ለአፍታ እንኩዋን የማትጎድል ለሰው ሙላቱ ነህ አንተን ነው እንጂ ጥብቅ አድርጎ መያዝ ያዘኝ እያሉ ማልዶ በጠዋት በአንተው እጅ ደምቆ መዋል ደጅ እየጠኑ አንተን ነው እንጂ ጥብቅ አድርጎ መያዝ ያዘኝ እያሉ ማልዶ በጠዋት በአንተው እጅ ነቅቶ መዋል ደጅ እየጠኑ አይኔን ጉዳዬ ላይ ማድረግ ፍለጋዬን እድሜ ልክ መፈለግ ናፍቆቴን ሳላርፍ መናፈቅ ጉጉቴን ሳልደክም መፈለግ እንዲሆንልኝ ይብዛልኝ ጸጋህ ጊዜው ደርሶ እስክደርስ አንተ ጋ ገባ ወጣ እግሬ ሳይልብኝ ፍለጋዬ ሳትጎድል ብዛልኝ በድነቴ ጠዋት በገባኸኝ ማግስት ጨዋታ ወሬዬ መወደዴን ማድነቅ ዘምሬህ አልጠግብ አውርቼህ አልረካ ይቺህ ትንሽ ልቤ ለፍቅርህ ሸፍታ አልደግ አንተላይ እራሴን አልቻል አጓጉል ነው ሁሉም ያላንተ መች ያምራል መጠበቂያ አጥሬ መሰንበቻዬ ነህ ልኑር እንደፈዘዝኩ አይኔ አንተን እያለ ጉዳዬ አንተው ነህ መናፈቄ መምጣትህን ጉጉቴ አይኔ እስከሚያይህ ሁሌ ሁሌ ሁሌ አንተን ብቻ እስከ እድሜዬ መቋጫ ሁሌ ሁሌ ሁሌ ኢየሱስን ብቻ እስከ ዕድሜዬ መቋጫ ሁሌ ሁሌ ሁሌ አንተን ብቻ እስከ እድሜዬ መቋጫ ሁሌ ሁሌ ሁሌ አንተን ብቻ እስከ እድሜዬ መቋጫ አይኔን ጉዳዬ ላይ ማድረግ ፍለጋዬን እድሜ ልክ መፈለግ ናፍቆቴን ሳላርፍ መናፈቅ ጉጉቴን ሳልደክም መፈለግ እንዲሆንልኝ ይብዛልኝ ጸጋህ ጊዜው ደርሶ እስክደርስ አንተ ጋ ገባ ወጣ እግሬ ሳይልብኝ ፍለጋዬ ሳትጎድል ብዛልኝ