Song Lyrics

ፈራ ፍርሃቴ

Fera Firhate

Aster Abebe
Hallelujah
ደረበልኝ በላይ አለበሰኝ ጸጋ እንዲሆነኝ አቅም እስክደርስ እርሱ ጋ በአቅመኞች ጉልበት በብርቱዎች ማደም የማትገፈፍ ልብሴ ለኔ እንዳንተ የለም ደረበልኝ በላይ አለበሰኝ ጸጋ እንዲሆነኝ አቅም እስክደርስ እሱ ጋ በአቅመኞች ጉልበት በብርቱዎች ማደም የማትገፈፍ ልብሴ ለኔ እንዳንተ የለም 1- በህብሮች ቀለም በተንቆጠቆጠች ከወንድሞች መሃል ለዮሴፍ ለተባለች ቢውልባት ደምቆ ለብሶ ቢያምርበት ቢያሳብቅ ሞገሱን አይንህ እንዳረፈበት ዛቻ ሲጠብቀው መልካም እያሰበ እንጀራ አቀብሎ ጉድጓድ ለተቸረ ለሰው ሃገር ሰዉ ጠብቀህ ዘመንን በአንተው እጅ ለበሰ የማይገፈፈውን 2- የንጉስ ልብ ከፍቶ ጦርን ሲወረውር የተቀባው ቅባት ሲያስነሳ ስደትን በእባብ ጊንጥ መኖሪያ በአዶላም ዋሻ ስንቱን አስጀገነ ሆነኸው ድል መንሻ መጠጊያ ለሌለው ማስገቢያ ለአንገቱ ስንቱ ተማምኖብህ ተረፈ ለስንቱ ሸለቆው ጠገበ በጠልህ ረስርሶ ቀን እስኪወጣለት አንተን ተንተርሶ ፈራ ፍርሃቴ ቃልህን ስትናገር ሸሸ ጨለማዬ ነጋ በእኔ መንደር ጥንካሬ አገኘኝ ፊትህን በማየት ደመቀ ህይወቴ ከአንተ በመቆየት ፈራ ፍርሃቴ ቃልህን ስትናገር ሸሸ ጨለማዬ ነጋ በኔ መንደር ጥንካሬ አገኘኝ ፊትህን በማየት ደመቀ ህይወቴ ከአንተ በመቆየት ከላይ ከውሽንፍር ጥላ ከሃሩሩ የጸናልኝ ቤቴ መርከብ በማዕበሉ የማይደፈር አጥር ለጎመጀኝ አውሬ ትልቁን ወግድ ባይ የማይነቀነቅ በሬ ከላይ ከውሽንፍር ጥላ ከሃሩሩ የጸናልኝ ቤቴ መርከብ በማዕበሉ የማይደፈር አጥር ለጎመጀኝ አውሬ ትልቁን ወግድ ባይ የማይነቀነቅ በሬ አዎ ስምህ ነው አዎ አዎ ስምህ ነው አዎ አዎ ስምህ ነው አዎ አዎ ስምህ ነው አዎ ምን ይሆናል ለጸጋው ታልፎ የተሰጠ መንገድ ጎዳናውን ለእግዚአብሔር ይኸውልህ ያለ ምን ይሆናል ለጸጋው ታልፎ የተሰጠ መንገድ ጎዳናውን ለእግዚአብሔር ይኸውልህ ያለ ያየህለት እንጂ የሚያልፍ የሚያገድመው አያገኘው ቃሉ እንዳለ እንደተጻፈለት ነው የሚኖረው ያየህለት እንጂ የሚያልፍ የሚያገድመው አያገኘው ቃሉ እንዳለ እንደተጻፈለት ነው የሚኖረው አዎ ስምህ ነው አዎ አዎ ስምህ ነው አዎ አዎ ስምህ ነው አዎ አዎ ስምህ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection