ቤቴን በሠላም በደግነትህ ሕይወቴን ሞላው ድንቅ በረከትህ (x2) አልቆጥብ አልቀንስ አሀሀ ያረከውን ላውራ አሀሀ ታምራትህ በዝቷል የማዳንህ ሥራ(x2) በእንጀራና ውሃ ብቻ መች ይኖራል በዚህ ምድር ላይ ላይ ኧሄ ኧሄ የኔስ ልብ ምያርፈው የምያርፈው የሱን ክብር ሳይ (x2) ቤቴን በሠላም በደግነትህ ሕይወቴን ሞላው ድንቅ በረከትህ (x2) ሰው በሀብቱ ብዛት ለፍቶ ባከማቸው ሕይወቱ አይለካም አሄ አይለካም ድጋፍ በሚሆነው በእግዚአብሔር ይሻላል ቢመካ(x2) የነብሴን ረሀብ አሀሀ ብር ወርቅ ላይሞላው አሀሀ ሌትተቀን ብደክም ጎዶሎ ብዙ ነው (x2) (x2) ቤቴን በሠላም በደግነትህ ሕይወቴን ሞላው ድንቅ በረከትህ (x2) ማልጄ በፊቱ አምላኬ እለዋለሁ ባማረ ምስጋና አሄ ምስጋና አይጓደልበት አምልኮ ክብሩ የሱ ነውና (x2) ላንተ ይሁን አምልኮ ላንተ ይሁን ምስጋና (x2) ይገባሃልና ጌታዬ ይገባሃልና ይገባሃልና ወዳጄ ይገባሃልና