Song Lyrics

ተመቸኝ ቤትህ

Yosef Ayalew
Sirayen Yeserahilign
ሥምህ ጋሻዬና ከለላዬ ሆኖልኛል ጌታ በዘመኔ ሳልሰጋ እኖራለው ልቤ እርፎ በኃያሉ ክንድህ ተደግፎ (2x) ክበር አንተ ብቻ (2x) የለህ አቻ ንገሥ አንተ ብቻ (2x) የለህ አቻ ግዛኝ አንተ ብቻ (2x) የለህ አቻ አዝ፦ ተመቸኝ ቤትህ ተመቸኝ ተመችኝ ጉያህ ተመቸኝ አልመለስም ወደ ኋላ የግብጽን ሽንኩርት ላልበላ ቃልኪዳን ገባሁ ለእራሴ አመልክሃለሁ ኢየሱሴ (2x) እንደሚፈስ ዘይት ነው ሥምህ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ እኔም አንተን አንተኑ ብያለሁ ስምህን ላከብር ይሄው ቆሜያለሁ (2x) ክበር አንተ ብቻ (2x) የለህ አቻ ንገሥ አንተ ብቻ (2x) የለህ አቻ ግዛኝ አንተ ብቻ (2x) የለህ አቻ አልመኝ ከአንተ በስተቀር አያምረኝም ያለው በምድር ቀምሼ አውቄሃለሁ ምርጫዬ አድርጌሃለሁ የሕይወቴ መደምደሚያ ነህ ዘለዓለም ጌታዬ ትበቃኛለህ (2x) ክበር አንተ ብቻ (2x) የለህ አቻ ንገሥ አንተ ብቻ (2x) የለህ አቻ ግዛኝ አንተ ብቻ (2x) የለህ አቻ አዝ፦ ተመቸኝ ቤትህ ተመቸኝ ተመችኝ ጉያህ ተመቸኝ አልመለስም ወደ ኋላ የግብጽን ሽንኩርት ላልበላ ቃልኪዳን ገባሁ ለራሴ አመልክሃለሁ ኢየሱሴ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection