Song Lyrics

ላይጨልምብኝ

Yosef Ayalew
Sirayen Yeserahilign
ላይጨልምብኝ አንዴ አብርቶት ጌታ ነገሩን ሁሉ ገልብጦ (2x) ያለፈውን እንዳላስበው እንቅፋቶቹን አነሳሳቸው (2x) ጨለማዬን አበራኸው እንደፈሳሽ አሳለፍከው ጐህ ቀደደ ቀን ሊወጣ ማረፊያዬ ዘመን መጣ መኖሪያዬ አንተ ሆንክልኝ ከጭንቀቴ አሳለፍከኝ/ገላገልከኝ (2x) ተባረክ ጌታዬ ተባረክ ተባረክ ኢየሱሴ ተባረክ (2x) እስኪ ደጋግሜ ስምህን ልባርከው እንደአንተ ያለ ጌታ በዐይኔ ስላላየሁ ቀስቃሽ አልፈልግም አንተን ለማመስገን ታሪክ ያለኝ ሰው ነኝ ከፍ በል እግዚአብሔር ከፍ በል እግዚአብሔር (2x) ከፍ በልልኝ ጌታ ከፍ በልልኝ ከፍ በልልኝ ኢየሱስ ከፍ በልልኝ (2x) ከፊት ከፊቴ ጌታዬ ወጣና እሾሁን ሁሉ አነሳሳና (2x) አደላደለው ሕይወቴ ቀና ይመራኝ ጀመር በድል ጐዳና (2x) እረዳቴ ሆነህልኝ ተሸክመህ አሻገርከኝ አልነደፈኝ እባብ ጊንጡ መች አገኘን እንደ ምኞቱ ከፍ ላድርግህ ቸር ጌታዬ ደስ ያሰኝህ ምሥጋናዬ (2x) ተባረክ ጌታዬ ተባረክ ተባረክ ኢየሱሴ ተባረክ (2x) እስኪ ደጋግሜ ስምህን ልባርከው እንደአንተ ያለ ጌታ በዐይኔ ስላላየሁ ቀስቃሽ አልፈልግም አንተን ለማመስገን ታሪክ ያለኝ ሰው ነኝ ከፍ በል እግዚአብሔር ከፍ በል እግዚአብሔር (2x) ከፍ በልልኝ ጌታ ከፍ በልልኝ ከፍ በልልኝ ኢየሱስ ከፍ በልልኝ (2x) ያ ደመና እንዳያልፍ የለም ሲያስገመግም ጠላቴም ሲለኝ የሚያድንህ የለም ኧረዳቴ ግን እጁን ዘረጋ ከሰማያት እኔን ሊያወጣ ፈጥኖ ከሞት አንተ ስለእኔ ያልሆንከው ምን አለ (2x) ጌታ ስለእኔ ያልሆንከው ምን አለ ኢየሱስ ስለእኔ ያልሆንከው ምን አለ ምን ልበልህ ኧረ እኔ ምን ልበልህ ምን ልበልህ ጌታዬ ምን ልበልህ ምን ልክፈልህ ኧረ እኔ ምን ልክፈልህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection