Song Lyrics

ቆጠርከኝ

Yosef Ayalew
Sirayen Yeserahilign
አዝ፦ ቆጠርከኝ እንደ ባለማዕረግ ሳልለፋ ምንም ሳላደርግ ምህረትህ በዝቶልኝ በላዬ ኧረ ደግ እኮ ነህ ጌታዬ ልናገር እኔስ ቸርነትህን አላውቅም ክፉ መሆንህን (2x) እኔማ ይገርመኛል ሁልጊዜ ይደንቀኛል እኔማ ይገርመኛል ሳስበው ይደንቀኛል ሹመት ሆኖልኝ ነው ከዓለም የተወሰነ ማንም የማይቀያይረው ከላይ የሆነ ልጄ ነህ ብሎኛል ምን ልበል ይህ ማዕረጌ ነው ውስጤን መደነቅ ሞልቶታል ለእኔ በሆነው እኔማ ይገርመኛል ሁልጊዜ ይደንቀኛል እኔማ ይገርመኛል ሳስበው ይደንቀኛል አዝ፦ ቆጠርከኝ እንደ ባለማዕረግ ሳልለፋ ምንም ሳላደርግ ምህረትህ በዝቶልኝ በላዬ ኧረ ደግ እኮ ነህ ጌታዬ ልናገር እኔስ ቸርነትህን አላውቅም ክፉ መሆንህን በህልሜ በእውኔ አስቤ የማላውቀውን ብዙ አድርገህልኛል ያልጠበኩትን ልዘምር በገናዬን ላንሳ ቅኔን ልደርድር ግሩምና ድንቅ የሆነውን ስራህን ልናገር እኔማ ይገርመኛል ሁልጊዜ ይደንቀኛል እኔማ ይገርመኛል ሳስበው ይደንቀኛል አዝ፦ ቆጠርከኝ እንደ ባለማዕረግ ሳልለፋ ምንም ሳላደርግ ምህረትህ በዝቶልኝ በላዬ ኧረ ደግ እኮ ነህ ጌታዬ ልናገር እኔስ ቸርነትህን አላውቅም ክፉ መሆንህን አይቆጠር እንዲሁ አይባል ቸርነትህ የማይለወጠው ፍቅርህ የአባትነትህ ኧረ እንዴት ብዬ እገልጸዋለው ያረክልኝን ከቁጥር በላይ የበዛው የዋልክልኝን እኔማ ይገርመኛል ሁልጊዜ ይደንቀኛል እኔማ ይገርመኛል ሳስበው ይደንቀኛል አዝ፦ ቆጠርከኝ እንደ ባለማዕረግ ሳልለፋ ምንም ሳላደርግ ምህረትህ በዝቶልኝ በላዬ ኧረ ደግ እኮ ነህ ጌታዬ ልናገር እኔስ ቸርነትህን አላውቅም ክፉ መሆንህን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection