Song Lyrics

ሥራዬን የሠራህልኝ

Yosef Ayalew
Sirayen Yeserahilign
አዝ፦ ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ (2x) አማኑኤል ከፍ በልልኝ (3x) ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ የእኔ ጌታ ከፍ በልልኝ ተራራውን ንዶ ሜዳ ከአደረገው መራመድ ብቻ ነው ከእኔ ሚጠበቀው (2x) ጐዳናዬ ቀንቶ ተራመድ ብሎኛል ከእኔ ጋር ስላለ ማን ይቃወመኛል (2x) ማን ይቃወመኛል (2x) የቱ ይይዘኛል (2x) አልፈራም ልቤ አይሰጋ ጌታዬ አለ ከእኔ ጋ አልፈራም ልቤ አይሰጋ የጠራኝ አለ ከእኔ ጋ አይቆምም ምንም ከፊቴ እግዚአብሔር ነው ዛሬም ጉልበቴ (5x) አዝ፦ ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ (2x) አማኑኤል ከፍ በልልኝ (3x) ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ የእኔ ጌታ ከፍ በልልኝ ሰባሪው እግዚአብሔር ከፊት ወጥቷልና ሃሳቤ ተሳክቶ መንገዴም ተቃና (2x) የነሃሱን ደጆች በስልጣን ሰበረው እኔም ሰባብሬ ከእርሱ ጋር አልፌያለው (2x) ከእርሱ ጋር አልፌያለው (4x) አልዝልም እኔ አልደክምም ስራዬ አያሰለችም (2x) ቅባቱ በእኔ ስላለ ይሄዳል እየጀመረ (5x) አዝ፦ ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ (2x) አማኑኤል ከፍ በልልኝ (3x) ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ የእኔ ጌታ ከፍ በልልኝ ታማኝ ነው የጠራኝ ጌታ ለምንም ትጥቄ አይፈታ (2x) ብርቱ ነው በቃሉ የፀና ይመራኛል በድል ጐዳና (5x) አዝ፦ ሥራዬን የሠራህልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ (2x) አማኑኤል ከፍ በልልኝ (3x) ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ የእኔ ጌታ ከፍ በልልኝ ከፍ በል ብል ሁልጊዜ ኢሄ መች ይበቃሃል (3x) ተባረክ ብል ሁልጊዜ ኢሄ መች ይበቃሃል (3x) ተመለክ ብል ሁልጊዜ ኢሄ መች ይበቃሃል (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection