Song Lyrics

ሰው አይረሳም

Yosef Ayalew
Sirayen Yeserahilign
አዝ፦ ሰው አይረሳም ጌታ ሰው አይረሳም ኢየሱስ (2x) እንደ ሰው አይደለም ጌታ እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (2x) ፍቅሩ አይቀዘቅዝ ወረት አያውቀው እንደ ጌታ ያለ የትም አይገኝም የተናገረውን ቃሉ ይፈጽማል ተናግሮ ማድረግ እርሱ ብቻ ያውቃል አዝ፦ ሰው አይረሳም ጌታ ሰው አይረሳም ኢየሱስ (2x) እንደ ሰው አይደለም ጌታ እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (2x) ማክበርና ማንሳት ጌታ ያውቅበታል እርሱን የተጠጋ የቱ መሽቶበታል እንደ ንጋት ብርሃን ክብሩ እየጨመረ አቀማጥሎ ያኖራል እንዲህ እያከበረ አዝ፦ ሰው አይረሳም ጌታ ሰው አይረሳም ኢየሱስ (2x) እንደ ሰው አይደለም ጌታ እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (2x) የቱነው የተረሳ ማነው የሚጸጸት ሳይታሰብ ኖሮ ጊዜው ያለፈበት የተጣለው ይልቅ ከፍ ከፍ አድርጐ ደስታ ይሰጠዋል እንባን ከዓይኑ ጠርጐ አዝ፦ ሰው አይረሳም ጌታ ሰው አይረሳም ኢየሱስ (2x) እንደ ሰው አይደለም ጌታ እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (2x) አይጠረጠርም ይታመናል እንጂ እንኳን ቤቱ ኖሮ አድጐ በእርሱ እጂ ያሳልፍለታል ዘመኑን በተድላ እርዳኝ ብሎ መጥቶ የቱ ሰው ተጐዳ አዝ፦ ሰው አይረሳም ጌታ ሰው አይረሳም ኢየሱስ (2x) እንደ ሰው አይደለም ጌታ እንደ ሰው አይደለም ኢየሱስ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection