Song Lyrics

ሰማይ ምን አለ

Yishak Sedik
Special Edition
ሰማይ ምን አለ ነው እኛ የምንለው አዝማች/አምላክ አለንና አለት አቋም አለው ጌታ ላይ የፀና ቃሉ ላይ የፀና መሰረቴ የሆነው አለቴ ኢየሱስ ነው የማልናወጥበት እምነቴ ክርስቶስ ነው ማነው x2 እኔን የሚያስፈራው የቱስ ነው ምንድነው ልቤን የሚያሰጋው እኮ ማነው x2 እኔን የሚያስፈራው የቱስ ነው ምንድነው ልቤን የሚያሰጋው ልቤ ፅኑ ነው x8 ማዕበል የለም አልልም ወጀቡም አይካድም የቱም ቤት የክረምት ዝናብ ጎርፍ አይቀርለትም በዚች አለም ሳለን መከራ የለብንም አንልም ዳሩ ግን በክርስቶስ ሆነን ከቶ አንሸነፍም መታመኛ ትምክቴ ቀን ሳለ የቆምኩበት በኢየሱስ ነው የማይፈራው በእርግጥ ከተመሰረቱበት መታመኛ ትምክቴ ቀን ሳለ የቆምኩበት በኢየሱስ ነው የማይሰጋው በእርግጥ ከተመሰረቱበት መሰረቴ የሆነው አለቴ ኢየሱስ ነው ልቤ ፅኑ ነው ሰማይ ምን አለ ነው ቤት በይድረስ ተሰርቶ ምን ቢያምር አያዘልቅም አወዳደቁ አይጣል ነው ዶፍ አይቋቋምም አሸዋ መቆሚያ አይሆንም ህይወት አይመሰርትም ከአለቱ በቀር አፅንቶ የሚያዘልቅ አይገኝም ክፋ ቀን ማለፊያ ቤቴን የያዘ ቀጥ አድርጎ ኢየሱስ ነው የሚያድን ከመከራ ሸሽጎ መሰረቴ ነው አለቴ ነው x4 መሰረቴ የሆነው አለቴ ኢየሱስ ነው x2 ልቤ ፅኑ ነው!
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection