Song Lyrics

ይህ ነው ፀሎቴ

Yishak Sedik
Special Edition
ይህ ነው ፀሎቴ የማይቀየረው ምንም ቢሰጠኝ እጄ ማይለቀው ጠብቄ የያዝኩት እንደ ቀሪ ሀብት ራሴን ማገኘው ሁሌም በአንተ ፊት አንተን ፈልጌህ ነው!!! የምታስፈልገኝ አንተው ነህ እኔ ምፈልገው አንተን ነው እህል ውሃ አይደለም ወይም መጠለያ ለዘላለም አንተው ነህ የእኔ መኖሪያ የምታስፈልገኝ አንተው ነህ እኔ ምፈልገው አንተን ነው ቃልህ ህይወቴ ነው ፊትህ ብርሃኔ ኢየሱስ በአንተ ነውና የሆነው መዳኔ የምታስፈልገኝ አንተው ነህ እኔ የምፈልገው አንተን ነው ይህ ነው ፀሎቴ የማይቀየረው ምንም ቢሰጠኝ እጄ ማይለቀው ጠብቄ የያዝኩት እንደ ቀሪ ሀብት ራሴን ማገኘው ሁሌም በአንተ ፊት አንተን ፈልጌህ ነው!!! የምታስፈልገኝ አንተው ነህ እኔ የምፈልገው አንተን ነው በውድቀት ሌሊት ነፍስ ስጋዬ አርፈው መንፈሴ ግን ለአንተ ነቅቶ ነው ሚገኘው የምታስፈልገኝ አንተው ነህ እኔ የምፈልገው አንተን ነው አለምን ያስንቃል ሀልዎትህ ገዝቶ ካንተ ያጣብቃል ህይወት ሰማይ ገብቶ የምታስፈልገኝ አንተው ነህ አንዴ ይነደሉ ቀላያት ያፍስሱ በህይወት ውሃ ወንዝ ነፍሳት ይረስርሱ ሰማይ ሰማያት በቃ ይከፈቱ አንተን ለማግኘት ነው የትውልድ ናፍቆቱ እኛ የምፈልገው አንተን ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection