እኔ ግን ኣምላኬ ባንተ ደስ ይለኛል ሃሴት ሆነህልኛል ምህረትን ታምኖ ልቤን ኣርፎብሃል ሰላሜ ሆነሃል x2 ውስጤ ኣርፎብሃል ደስታየ ሆነሃል ልቤ ጸንቶብሃል በለስ እንዃን ባታፈራ ቢጎድል የወይራ ስራ እርሾችም መብል ባይሰጡ ምንም ባይገኝ በጋጡ እኔ ግን ኢየሱስ ባንተ ደስ ይለኛል ሃሴት ኣደርጋለው ሃይል ሆነህልኛል ኣምላኬ ሆይ ወዳንተ መቅረብ ይሻለኛል ያላንተ ዓለም ትርፉ ሃጥኡ ምኑያስቀናል ወደመቅደስ ገብቼ ክብርህን ኣግኝቶኛል በጽድቅፊት ሆናለው ደስታህንይበቃኛል ኣንተ የሌለህበት ጥጋብ ተድላና ፍስሀ ተጠምቶ እንደ መቃጠል ነው በደረቅ በርሀ ልዩነቴ እኮ ነህ ጌታ ኣለመኞች ያጡህ የምታረካ የህይወት ውሃ ነህ ለጠጡህ