Song Lyrics

ኢየሱስ ነክተኸኛል

Yidnekachew Teka
Special Edition
ቶሎ ቶሎ ያረጅብኛል የምሰማው ሚያወሩኝ በዙሪያዬ መቼም መቼም ማታረጅብኝ ኢየሱስ ነህ ያንተ ክብርህ ጌታዬ ወዲያው ወዲያው ይሰለቸኛል የምሰማው ሚወራው በዙሪያዬ መቼም መቼም ማታረጅብኝ ኢየሱሴ ያንተ ክብር ጌታዬ ልቤን ማሰንበት የቻልከው አንተ ነህ/2*/ አንተ ነህ/2*/ ኢየሱስ ነህ/2*/ በምን አይነት ፍቅር እንደነካኸኝ እኔ እንጃ/4*/ ምንም ነገር እንዳይገርመኝ አድርገህ ነክተኸኛል ወደ ልቤ ገብተህ መገረሚያዬን ቀየርክብኝ በቃ ኢየሱስ ሆነህ የልቤ አለቃ በምን አይነት ፍቅር እንደነካኸኝ እኔ እንጃ/2*/ በምን አይነት መንካት እንደነካኸኝ እኔ እንጃ/4*/ እኔ እንጃ/2*/ እኔ እንጃ ከአይምርዬ በላይ እኔ እንጃ እኔ እንጃ መግለጥ አልችልም እኔ እንጃ እኔ እንጃ ቃላት የሉኝም እኔ እንጃ እኔ እንጃ የኢየሱስ ፍቅር እኔ እንጃ ኢየሱስ ኢየሱስ ልክ እንደ ልጁ ልክ እንደ ህፃን ሕልውናህ ያደርገኛል አንዴ መሳቅ አንዴ ማልቀስ በክብርህ ፊት ያሰኘኛል ፊቴን ካንተ ካንተ አዙሬ መቆየት እኔ አልችልም ቶሎ ግባ ግባ ይለኛል ኢየሱስ ፊትህ ይርበኛል ልቤን ማሰንበት የቻልከው አንተ ነህ/2*/ ልቤ ውሰጥ መሰንበት የቻልከው አንተ ነህ እኔ ውስጥ መሰንበት የቻልከው አንተ ነህ አንተ ነህ/2*/ ኢየሱስ ነህ/2* በምድር ላይ ደስ የሚለኝ ነገር ቢኖር አንተን ማምለክ ነው ጌታዬ አንተን ማምለክ ነው ኢየሱሴ ኸረ አንተን መውደድ ወዳጄ አንተን መውደድ ነው ኢየሱሴ በምድር ላይ ደስ የሚለኝ ነገር ቢኖር አንተን ማፍቀር ነው ወዳጄ አንተን ማፍቀር ነው ኢየሱስ ፍቅርህ ነክቶኛል ምን አደርጋለሁ እጄን ዘርግቼ አመልክሀለሁኝ/2*/ ፍቅርህ ነክቶኛል ምን አደርጋለሁ በፍፁም ልቤ አመልክሀለሁኝ በፍፁም ነፍሴ አመልክሀለሁኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection