ሌላ ምወድበት ትርፍ አካል ከየት ላምጣ ታዲያ መውደጃዬ ሁሉ ወሰድከው ሆኜ የፍቅርህ ባሪያ ፍቅሬን አንጠፍጥፌ አንተ ላይ እጨርሰዋለው እራስህ ላይ*2 ፍቅሬን አንጠፍጥፌ አንተ ላይ እጨርሰዋለው እግሮችህ ላይ ዙፍንህ ላይ አንተ ላይ ምህረትህ ላይ እራስህ ላይ የፍቅሬ ጥግ ነህ የኔ መዳረሻ የት ሄጄ ልተንፍስ ፍቅሬን ለማን ላውራ የፍቅር ቦታዬ ፍቅሬን ማውልብህ ኢየሱስ አለህልኝ ሁሌ እንድነግርህ ሌላ ቦታ የማፈሰው እንባ የለኝም ሌላ ቦታ የሚባክን ፍቅር የለኝም ባዕድ ሰፈር ሚባክን ፍቅር የለኝም ላልሞተለኝም ሚባክን ፍቅር (የለኝም)*4 ኢየሱስዬ ላይ አለቀብኝ የኔ ኢየሱሴ ላይ ፍቅሬን ጨረስኩኝ ማንም ዋጋ ከፍሎ አልሞተም ለምኔም ስለ እኔ አንተ አይደለህም ወይ ኢየሱስ የህይወቴ ዋሴ ሌላ ምወድበት ትርፍ አካል ከየት ላምጣ ታዲያ መውደጃዬ ሁሉ ወሰድከው ሆኜ የፍቅርህ ባሪያ ህይወቴን ተማምለዋል ሊያደርጉኝ የራሳቸው ሊወስዱኝ ተፎካክረዋል እጣ እየተጣጣሉ ከእነርሱ ከቶ አንዳቸውም እጣ ውስጥ በሞት አልገቡም አንተ ነህ እራስህን ያስያዝከው በሞትህ ያሸነፍካቸው ታሪኬን ያሳመርከው ላይ ፍቅሬ ይለቅ አንተ ላይ ነገሬን ያሳመርከው ላይ ፍቅሬ ይለቅ አንተ ላይ ምሕረትህን ያገነንከው ላይ ፍቅሬ ይለቅ አንተ ላይ በሞት የታደገኸኝ ላይ ፍቅሬ ይለቅ አንተ ላይ ኢየሱስ*4