Song Lyrics

ግን ባንተ

ደካማ ሆኜ አገኘኸኝ ኃጥያተኛ ሆኜ አገኘኸኝ የማልጠቅም ሆኜ አገኘኸኝ ከሰይጣን እጅ ሆኜ አገኘኸኝ ግን ባንተ ከዚህ ሁሉ ወጥቻለሁ ግን ባንተ የእግዚአብሔር ልጅ ተብያለሁ ግን ባንተ ከዚህ ሁሉ ወጥቻለሁ ግን ባንተ የእግዚአብሔር ልጅ ተብያለሁ ዛሬ አርገኸኛል የብርሃን ልጅ እኔን ኢየሱስ ወሰደህ ጨለማዬን/4*/ ይቺ ፅዋ ከኔ ትለፍ ብትል እንኳ ኢየሱስ ታዘአል እንዳያልፈኝ የሕይወት ፅዋ የእግዚአብሔር በግ አስቀድመህ የታረድከው ሌባው እንዳያርደኝ እንዳልጠፋ እንዳልሞት ነው ለምን ተውከኝ ብለህ ስትጮህ አብ ዝም ያለህ እኔ እንዳልጣል እንዳልተው ሁሌ ፊትህ ደዌ እመሜን ተቀበልህ ተሸከምህ እኔ ያንተን ሕይወት ደኅንነትን እንድቀበል የብርሃን መልዕክቴ ነህ ኢየሱስ ልቤ ላይ በራህ ሰማሁህ የምስራቼ ድኛለሁ ወንጌል ሰምቼ በአመድ ፈንታ ሆነኽልኛል አክሊሌ በለቅሶ ፈንታ የደስታ ዘይት ነሆ ለኔ በአዘን ፈንታ የደስታ መጎናፀፊያ አረከኝ እኔን የምሕረትህ ማሳያ ጋሽ ሆነህ ግን ተወጋህ ጎንህን እረኛ የሆንከው ልክ እንደ በግ ተነዳህ የአለም ጌታ በምድር ጌታ ፊት ቆመሀል ምንጭ የሆንከው አንተ የኔ ኢየሱስ ተጠምተአል እንደ ፀሐይ የሚያበራ ፊት እያለህ ግን እኔ እንዳበራ እንድደምቅ ተተፋብህ ሰማይ ምድርን የምትጠቀልል ልክ እንደ ጨርቅ ግን ኢየሱስ ለኔ ተጠቅልለህ መቃብር ሆንክ ይሁን ስትል የሚሆንልህ አንተ ላይ ይሁን አሉብህ ግን ዝም አልክ አልመለስክም አይተህ ነው እኔን ደስታህን ለወጉህ እጆች ኃይላቸው ነበርክ ፈጣሪ ለሰደቡህ አፎች አንተ ነህ የእነርሱ ሰሪ ፈቀድክላቸው አልከለከልካቸውም የምትሞተው በጦር ለወጉህ ለእነርሱም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection