አዝ:- ህልውናህ ከሕይወቴ እንዳይሄድብኝ አሜን መገኘትህ ከኑሮዬ እንዳይሄድብኝ አሜን አብሮነትህ ከዘመኔ እንዳይሄድብኝ አሜን መንፈስ ቅዱስ ከሕይወቴ እንዳትሄድብኝ አሜን የኔ ክብር ከኑሮዬ እንዳትሄድብኝ አሜን የኔ ሞገስ ከሕይወቴ እንዳትሄድብኝ አሜን አንተ የተከልከው ከልብ የማይጠፋ በውስጤ ረሃብ አለ ሚያስሮጠኝ አንተ ጋር ባልደርስብህ እንኳን ያስቆምሃል ረሃቤ ቀን ማታ እጮሃለሁ አትሂድብኝ ብዬ ተራርቄ መንፈስ ቅዱስ ከአንተ ጋራ የምለምደው ሕይወት የለኝ እኔስ ሌላ አያሽሽህ አያርቅህ ማንነቴ ታገስና እባክህ ኑር በሕይወቴ እንዳትሄድብኝ ከሕይወቴ እንዳትሄድብኝ ከኑሮዬ (2x) እንዳትሄድብኝ እንዳትሄድብኝ (4x) አዝ:- ህልውናህ ከሕይወቴ እንዳይሄድብኝ አሜን አባትዬ ከኑሮዬ እንዳትሄድብኝ አሜን የኔ ክብር ከዘመኔ እንዳትሄድብኝ አሜን እኔ አልችልም ያለ ክብርህ እንዳትሄድብኝ አሜን መንፈስህን ከሕይወቴ አትውሰድብኝ አሜን መገኘትህን ከኑሮዬ እንዳይሄድብኝ አሜን የሰው ልጅ ሲያሳካ የዛሬው ጭንቀቱን ይረሳዋል ደግሞ ሌላ ጥያቄውን አንተ ግን ከጐደልክ ከሰው ልጅ ሕይወት በምን ይረሳኸል ምን ያገኘ እለት ሞልቶ ጌታ በእጄ ያለው የሰጠኅኝ መቼም ቢሆን የአንተን ቦታ አይተካልኝ መንፈስ ቅዱስ የሸፈንከው ሰው አይወድቅም ሁሉ ቀርቶ አንተ ብቻ እትሂድብኝ (እንዳትሄድብኝ) እንዳትሄድብኝ ከሕይወቴ እንዳትሄድብኝ ከኑሮዬ (2x)