የሕይወቴ ክብር የመኖሬ ግብ ነህ ስራመድ ስቀመጥ ሁልጊዜ ማልምህ ኢየሱሴ እስኪ ልንገርህ የልቤን ካላሳይህ ከአንተ ውጭ የቱ ክብሬ ነው ሕይወቴን ልቤን ሚገዛው (2x) አዝ:- ኧረ ይሄ ሰው ተባረከ ቢባል (2x) ምትቆጠርልኝ በረከቴ አንተው ነህ (4x) ኧረ ይሄ ሰው አደገ እንኳን ቢባል (2x) ምትቆጠርልኝ እድገቴ አንተው ነህ (4x) በሩቅ ያሉ ሁሉ ስለእኔ ቢያወሩ ቅርቤም ያሉ ሁሉ ስለእኔ ቢያወሩ አብረኸኝ ተወራ/ተነገር ኢየሱስዬ ሰው የሆንኩብህ ነህ ቁም ነገሬ (2x) ምንም ታሪክ የለኝ ስለእራሴ አንተ ግን ተወራ ኢየሱሴ ብቻህን ደምቀህ ታይ አንተ በእኔ አዝ:- ኧረ ይሄ ሰው ተባረከ ቢባል (2x) ምትቆጠርልኝ በረከቴ አንተው ነህ (4x) ኧረ ይሄ ሰው አደገ እንኳን ቢባል (2x) ምትቆጠርልኝ እድገቴ አንተው ነህ (4x)