Song Lyrics

ማዳኑ ከፍ ያለ ነው

Yidnekachew Teka
Chekolebign Libe Liyagegnih
ይወርሰኛል ብዬ የፈራሁት ነገር የቆመ በበር አይሆንም አለ ጌታ ከሰማያት ቃል ወጣ ስለእኔ ራራልኝ ውዴ (2x) ወጀብ አለ ከፊት አትፍራ አለኝ ጌታዬ ተገልብጧል ነገሩ ቃል ወጥቷል ዛሬ ለእኔ በመንገድ ሊያስቀረኝ ሊገታኝ የነበረ ቀደምኩት አለኝ ጌታ ወጥመዱ ተሰበረ ማነው ማዕበሉን የገሰጸው ማነው ወጀቡን ጸጥ ያደረገው ማነው ይሁን ሲል ሚሆንለት ማነው የአፉ ቃል ሚጸናለት ጌታዬን ነው ጌታዬ ያየሁት በዘመኔ (2x) ፈርቶት የሩቅ ዘመኔን ቢነሳ ያ ጠላቴ ጉልበቴን ሊያደክመው ቢቆምም በመንገዴ ይሄዳል የኔ ነገር በቃል ሚኖር አይቆምም ሰባሪው ከፊት ወጥቷል ሰብሬ አልፋለሁ እኔ ማነው መንገዴን ያስጀመረኝ ማነው መንገዴን ሚያስጨርሰኝ ማነው ከፊቴ የቀደመው ማነው መንገዴን የከፈተው ጌታዬን ነው ጌታዬ ያየሁት በዘመኔ (2x) ንጉሥ ወርዶ ከሰማይ አይቆምም ፊቱ ከልካይ ይታደጋል ያድናል ደርሶ ከሞት ያወጣል እኔም የእርሱ ልጅ ሆኜ ድኛለሁ ከጠላቴ ጠላት ያሴረው ሴራ መና ሆነ ፉከራ ማዳኑ ከፍ ያለ ነው ኢየሱስ ከፍ ያለ ነው ሲረዳኝ ከፍ ያለ ነው ሲያወጣኝ ከፍ ያለ ነው ጌታ ሲረዳኝ ጌታ ሲያወጣኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection