ሰማይና ምድርን አጸና በቃሉ ምድርና ሞላዋን ሸፈነ በክብሩ ዐይኑን ከፍቶ ያየ እንዴት የታደለ የእግዚአብሔርን ጥበብ ክብሩን ያስተዋለ ሰማዩም ይናገር ምድሩም ይመስክር የግርማ ሞገሱን የውበቱን ንገር ሁሉን የፈጠረ ሁሉንም የሰራ ከእርሱ በቀር ማነው አዬ እስቲ ይናገራ መደርደር በገና እጄ ለምዶ ጀመረ ሊቀኝ እጄ ለምዶ ጌታን ወዶ አሄሄ (2x) መዘመር ለጌታ አፌ ለምዶ ጀመረ ሊቀኝ አፌ ለምዶ ጌታን ወዶ አሄሄ(2x) (ጌታን ወዶ) የገባዋል ብሎ (ጌታን ወዶ) ቅኔውን ፈልጐ (ጌታን ወዶ) ታዲያ ለማን ላዚም (ጌታን ወዶ) ጌታዬ አለ ብሎ (ጌታን ወዶ) አዬዬ ጌታን ወዶ አሀሀሀሀ (ጌታን ወዶ) ወዶ (ጌታን ወዶ) ጌታን ወዶ (ጌታን ወዶ) ቢሆንልኝማ እህህህ ክብርህ ሽልማቴ እህህህ ዘምሬ አልጠግበውም እኔማ እስከዘለዓለሜ ቢሆንልኝማ እህህህ ክብርህ ሽልማቴ እህህህ በዜማ ይሞላል የእኔ ቤት ቀንና ሌሊቴ ይሁን ስትለው ሁሉ ሆነ በአንደበትህ ቃል ተፈጠረ (2x) የሌለን ነገር ልክ እንዳለ አንተ ስትጠራው እውን ሆነ (2x) ባዶ የሆነው ምድረ በዳ ገነት ይሆናል ቃል ከወጣ (2x) የሞተ ነገር የቀበሩት ጌታ ስትጠራው ይላል አቤት (2x) በሉት (3x) ተባረክ በሉት በሉት (3x) ትልቅ ነህ በሉት በሉት (3x) ጌታን ልዩ ነህ በሉት በሉት (3x) ተባረክ በሉት በሉት ተባረክ በሉት በሉት ትልቅ ነህ በሉት በሉት ልዩ ነህ በሉት በሉት ጌታ ነህ በሉት በሕይወቴ አይተው ለወደድከው ነገር ልብህ ደስ ብሎት ስለእኔ ብትምል ምላሽ አለኝ ብለህ ከወደድክ ልትሰጠኝ ክብርህ ሽልማቴ አሄሄ ምነው በሆነልኝ ቢሆንልኝማ እህህህ ክብርህ ሽልማቴ እህህህ ዘምሬ አልጠግበውም እኔማ እስከዘለዓለሜ ቢሆንልኝማ እህህህ ክብርህ ሽልማቴ እህህህ በዜማ ይሞላል የእኔ ቤት ቀንና ሌሊቴ (2x)