በድካሜ ማግስት ፊትህን ልይ አልል ግን ውስጤ ናፍቆሃል ምን ብዬ ልናገር ፊትህ ተደፍቼ ማረኝ አልኩህና ትቼዋለሁ አልከኝ ቀና እረከኝና (2x) አቤቱ (3x) እንደአንተ የሚገባው የለም እንደ አንተ የሚሰማኝ የለም እንደ አንተ የሚወደኝ የለም እንደ አንተ ሚራራልኝ የለም (2x) በደል ፈጽሜ ፈርቼ መንገድ ስጀምር ልሸሽ ድንገት ናፍቀኀኝ መጥቼ ድፍረቴን ሲነሳኝ ድካሜ አንተ ነህ እጆቼን የያዝከው (የያዝከው) ምህረቴ ለአንተ ነው ያልከው መለስካት ሕይወቴን ወደ አንተ (ወደ አንተ) አልችልም በቃኝ ያለ አንተ ፊትህን ከሰወርክብኝ ደነግጣለሁ ዝም ካልከኝ ወደ ሞት ጉድጓድ ምወርድ እመስላለሁ ፈሪ ነኝ/እፈራለሁ ያለ ህልውናህ ውሎም ለማደር በርትቼም ደክሜም ቢሆን ምርጫዬ እግርህ ስር (2x) በረሃ ላይ በጥም ለከሰለ ፍቅርህን ተጠምቶ ለዛለ አባት ከደጃፍ ቆመሃል ልጅህን ለማየት ናፍቀሃል ደፍሬ አይደለም ወይ ንቂ ይሄውናኝ እስከ ድካሜ ያለ አንተ እንደማልችል አውቂ ወጣሁኝ አባቴን ብዬ ፊትህን ከሰወርክብኝ ደነግጣለሁ ዝም ካልከኝ ወደ ሞት ጉድጓድ ምወርድ እመስላለሁ ፈሪ ነኝ/እፈራለሁ ያለ ህልውናህ ውሎም ለማደር በርትቼም ደክሜም ቢሆን ምርጫዬ እግርህ ስር (2x) አቤቱ (3x) እንደአንተ የሚገባው የለም እንደ አንተ የሚሰማኝ የለም እንደ አንተ የሚወደኝ የለም እንደ አንተ ሚራራልኝ የለም