ጨምሮ ፍቅርህ በልቤ ሲገባኝ የመወደዴ ተራዬ ልኖር ለክብርህ ዘመኔን በቃ ልሰጥህ የፍቅር ምላሼ ሊሆንህ ደስ እንዲልህ ብዬ እጆቼን አንስቼ መጣሁ እሄውልህ ውዴ ተረታ ተረቱን ንቄ ወደ አንተ ስመጣ አንተን አይቼ እንጂ ኢየሱስ ሌላ ምን ፍለጋ (5x) አልገባኝም ነበር እኔ ያኔ ስትጠራኝ እወድሃለሁ እኔ ስትለኝ መች እንዲህ መሰለኝ ፊትህ ላይ እያነበብኩ ውዴ የፍቅር ፈገግታ ኢየሱስዬ ብዬ ወዲያው እጄን እስካነሳ አሳረፈኝ የፍቅር ፊትህ መቼም ቢሆን እስካይለየኝ ኢሄውና መላ ማንነቴ ንገሥበት ኢየሱስ አባቴ አዝ:- ኢየሱስ አንተ የኔ ኢየሱስ በአንተ አይደል ይህን ክብር ያየሁት ዛሬ ላይ ልቤን ሌላ ትምክት አይሞላም ኢየሱስ የኔ አባት የራሴ ትምክት እንዳይኖረኝ ምህረትህ እኔን ሰው አደረገኝ ትላንትን ሳየው ዛሬ ሆኜ አንተ ነህ እዚህ ለመድረሴ (4x) ለዓለም የቀረ ቦታ እስካይኖረኝ የፍቅሬን በኩር እንካ የልቤን በኩር እንካ ለራሴ የቀረ ቦታ እስካይኖረኝ የፍቅሬን በኩር እንካ የልቤን በኩር እንካ ለክብሬ የቀረ ቦታ እስካይኖረኝ የክብሬን በኩር እንካ ውሰደው እንካ እንካ የአንተ ነው እንካ እንካ ይነጠፍልህ እንካ ተራመድበት እንካ ወደ እኔ ናበት እንካ ኦ የፍቅሬን በኩር እንካ ውሰደው (4x) አዝ:- (ውሰደው) ኢየሱስ አንተ የኔ ኢየሱስ (ውሰደው) በአንተ አይደል ይህን ክብር ያየሁት (ውሰደው) በእኔ ላይ ልቤን ሌላ ትምከት (ውሰደው) አይሞላም ኢየሱስ የኔ አባት (ውሰደው) የራሴ ትምክት እንዳይኖረኝ (ውሰደው) ምህረትህ እኔን ሰው አደረገኝ (ውሰደው) ትላንትን ሳየው ዛሬ ሆኜ አንተ ነህ እዚህ ለመድረሴ (4x)