Song Lyrics

ከፊቴ ሁን ኢየሱሴ

Yidnekachew Teka
Chekolebign Libe Liyagegnih
ናና ከፊት ሁን ኢየሱሴ ክብሬ ነህ አትሆንም ከኋላዬ (4x) በሰው መሃል ድፍረቴ በሰው መሃል ድምቀቴ በሰው መሃል ሕይወቴ በሰው መሃል ውበቴ (2x) በማይጠቅም በማይረባ ነገር ልለውጠው አልችልም የዘለዓለም ክብሬን እርሱ ነው ከመሬት አንስቶ ያሳመረው ሕይወቴን ሞገሱን አፍሶ ዛሬ ላየኝ ሰው ጌታ እንደዚህ ሰርቶ ማለት አልችልም እጄ አደረገችው እኔ አሳያለሁ ኢየሱስ ነው ብዬ አልደብቀውም ክብሬን ከኋላዬ በእርሱ እኮ ነው (በጌታ) ክብር ያየሁት (በጌታ) ያንን ዘመን (በጌታ) የረሳሁት (በጌታ) ሌላውን (በጌታ) ተቀየረ (በጌታ) ክብሬ ገብቶ (በጌታ) ቤቴ አማረ (በጌታ) ለክብሬ (አለኝ ዛሬ) ዝማሬ (አለኝ ዛሬ) ምሥጋና (አለኝ ዛሬ) ለጌታ (አለኝ ዛሬ) ኢሄው እልልታ (አለኝ ዛሬ) ኢሄው ምሥጋና (አለኝ ዛሬ) ኢሄው ሙገሳ (አለኝ ዛሬ) ኢሄው ለጌታ (አለኝ ዛሬ) (2x) የክብር የሞገስ አክሊሌ ኢየሱስ ሆኖ መጣልኝ ሊለውጥ ታሪኬን አይችልም ልቤም መራቅ ከእርሱ እንዴት ሊሆንለት ነው ዘንግቶት ሞገሱን ሙሽራ ጌጧን ደግሞ ዝርግፍ ጌጧን ትረሳለች ወይ ውብ ያደረጋትን እርሷ ካልረሳች እኔ እንዴት ብዬ ነው ውብ ያደረገኝን ኢየሱስን ምረሳው በእርሱ አይደል ወይ (በጌታ) ክብር ያየሁት (በጌታ) ያንን ዘመን (በጌታ) የረሳሁት (በጌታ) ሌላውን (በጌታ) ተቀየረ (በጌታ) ክብሬ ገብቶ (በጌታ) ቤቴ አማረ (በጌታ) ለክብሬ (አለኝ ዛሬ) ዝማሬ (አለኝ ዛሬ) ምሥጋና (አለኝ ዛሬ) ለጌታ (አለኝ ዛሬ) ኢሄው እልልታ (አለኝ ዛሬ) ኢሄው ምሥጋና (አለኝ ዛሬ) ኢሄው ሙገሳ (አለኝ ዛሬ) ኢሄው ለጌታ (አለኝ ዛሬ) (2x) ልቤ እምቢ ይለኛል (ሌላ) አላይ ወደ ኋላ (ሌላ) ዓለም አትናፍቀኝ (ሌላ) ኢየሱሴን ብቻ (ሌላ) (2x) ለክብሬ (አለኝ ዛሬ) ዝማሬ (አለኝ ዛሬ) ምሥጋና (አለኝ ዛሬ) ለጌታ (አለኝ ዛሬ) ኢሄው እልልታ (አለኝ ዛሬ) ኢሄው ምሥጋና (አለኝ ዛሬ) ኢሄው ሙገሳ (አለኝ ዛሬ) ኢሄው ለጌታ (አለኝ ዛሬ) (2x) አለኝ (አለኝ ዛሬ) እህህህ (አለኝ ዛሬ) አለኝ (አለኝ ዛሬ) (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection