በፈረስ ውድድር ወደ ትልቁ ሜዳ ሁሉም ተሰማርቶ በድንገት ድል ቢነሳ ተብሎ ቢጠየቅ ማነው ያሸነፈው ፈረስና ጌታው አንድ ላይ ተቀምጠው እኔ ነኝ ሚለውን እስኪ ይጠየቅ ማነው ጌታው አይደለም ወይ ፈረሱን እያየሁ እንዲህ ሲል ሰማሁት እንዲህ ሲል አምላኬ ድል አድርጌያለሁኝ እኔማ በራሴ ስለዚህ ስንኖር በዚህች ምድር ላይ አምላክ እንዳለው ሰው እንደ ተወካይ ስለእኛ ለሞተው ደግሞ ለተነሳው የእርሱን ክብር አንጂ የእኛን ስራ እንርሳው አዝ:- ክብር ይሁን ለዝናው ክብር ይሁን ለስሙ ክብር ይሁን ዘለዓለም ክብር ይሁን ለተገባው (2x) በሩጫም ውድድር ወደ ሩጫው ሜዳ ሁሉም ተሰማርቶ በድንገት ድል ቢሰማ ቶሎ የሚይዙት ሮጠው ይሄዱና ባንዲራውን አይደል ሚለብሱት በተርታ የወከላቸውን አገር መቼ ረሱ ለስማቸው ብቻ አይሮጡም እነርሱ እንዲህ ሲል ሰማሁት እንዲህ ሲል አምላኬ ድል አድርጌያለሁኝ እኔማ በራሲ ስለዚህ ስንኖር በዚህች ምድር ላይ አምላክ እንዳለው ሰው እንደ ተወካይ ስለእኛ ለሞተው ደግሞ ለተነሳው የእርሱን ክብር አንጂ የእኛን ስራ እንርሳው??? አዝ:- ክብር ይሁን ለዝናው ክብር ይሁን ለስሙ ክብር ይሁን ዘለዓለም ክብር ይሁን ለተገባው (2x) የኔ ጌታ መሆን ያማረኝ የኔ ኢየሱሴን ስኖር በምድር የኔ ጌታ በእኔ አልፈህ ሁንብኝ የኔ ኢየሱስ ኢየሱስ ??? (2x) ኢየሱስ ተቀምጦባት በዛች ውርንጩላ ወደ ኢየሩሳሌም በክብር ሲገባ ሆሳዕና ሲባል ሲዘመር ለክብሩ ዘምባባው ሲነጠፍ ሁሉም ሆሆ እያሉ ብትረግጠውም እንኳን ውርንጭላዪቱ ያነጠፉላትን ሲገባ ንጉሡ ለእርሱ አይደል ወይ ያ ሁሉ ሙገሳ በፊት ማን አይቷታል ባለችበት ታስራ እኛንም ኢየሱስ ከፈታልህ ክብሩን ልቡ ከወደደህ ሊሰራብህ እርሱ ጌታ መርጦን እንጂ ምን ተገኝቶ ከኛ የማንጠቅም ባሪያዎች አይደለንም እኛ አዝ:- ክብር ይሁን ለዝናው ክብር ይሁን ለስሙ ክብር ይሁን ዘለዓለም ክብር ይሁን ለተገባው (2x) ሁለት ባሮች ታግለው በጥንቱ ጨዋታ አንደኛው ሲሸነፍ አንዱ ድል ሲነሳ ህዝቡ ይነሳና ለአሸናፊው ጌታ ይጨፍርለታል ባሪያው እየሰማ ምንም ቢያሸንፍ ባሪያው በጉልበቱ ጌታው ዋጋ ከፍሎ አድርጐታል የራሱ እንዲህ ሲል ሰማሁት እንዲህ ሲል አምላኬ ድል አድርጌያለሁኝ እኔማ በራሴ ስለዚህ ስንኖር በዚህች ምድር ላይ አምላክ እንዳለው ሰው እንደ ተወካይ ስለእኛ ለሞተው ደግሞ ለተነሳው የእርሱን ክብር አንጂ የእኛን ስራ እንርሳው??? አዝ:- ክብር ይሁን ለዝናው ክብር ይሁን ለስሙ ክብር ይሁን ዘለዓለም ክብር ይሁን ለተገባው (2x)