Song Lyrics

ባለ ዕዳ ነኝ

Yidnekachew Teka
Chekolebign Libe Liyagegnih
የደህንነቴ መደምደሚያ የክብር ስሜ ነህ መጠሪያ ማዕረጌ ሆነህ በሞትህ እኔም ተባልኩኝ ልጅህ (2x) የሞትህ ፍሬ የድካምህ በጣር የወለድከኝ ልጅህ በመከራ አልፈህ ያገኘኀኝ የዕንባህ ልጅህ ነኝ (2x) አዝ:- እኔ ባለ ዕዳ ነኝ እኔ የፍቅርህ ባለ ዕዳ ውለታህ ያለብኝ እንዴት እንዴት ብዬ ነው መክፈል የምችለው የፍቅርህን ሸክም መቼም የማልመልሰው ልክፈል እንኳን ብዬ ብጀምር ማለዳ ፍቅርህን እንዲያው ሰጥተኀኛል ታዲያ አይደለሁም ወይ የፍቅርህ ባለ ዕዳ መራመድ አይችሉም እግሮቼ ኢየሱስ በፍቅርህ ተይዤ እንዳልሄድ ከቶ ወደሌላ አርገኝ የፍቅርህ እስረኛ አርገኝ የፍቅርህ እስረኛ እንዳልሄድ ከቶ ወደሌላ ኢየሱስ በፍቅርህ ተይዤ መራመድ አይችሉም እግሮቼ አዝ:- ንግሥና መጣ በደምህ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ ክህነቱም መጣ በሞትህ ኧረ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ ደኸንነት ሆነ በጸጋህ እኔ ባለ ጸጋ ነኝ ልጅ መባል ቢሆን በስራህ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ የፍቅርህ ባለ ዕዳ የምህረትህ ባለ ዕዳ ነኝ መራመድ አልችልም እግሬ ተይዣለሁ እኔ ነፍሱን ለወዳጁ ሚሰዋ ይገኝ ይሆናል በመከራ ኢየሱስ የአንተ ግን ሚገርመው ለጠላትህ የሞትከው (2x) እድሜ ዘመኔን የሚገዛ ልቤን የያዘ ውለታህ የፍቅር ዕዳ አኖርክብኝ ሳልወድህ ወደድከኝ (2x) አዝ:- መልክና ውበትህ ጠፋ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ በሰው ተንቀህ ተተላህ ኧረ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ ተፈወስኩኝ አንተ ቆስለህ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ ደዌ ህመሜን ወሰድህ ኧረ እኔ ባለ ዕዳ ነኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection