ሁልጊዜ እኔ የሚገርመኝ ራሴን ሳየው ስቃኘው ኋላዬን በሄድኩበት በሕይወት መንገድ ያሳረፍከው አለ ምልክት ጌታ ኢየሱስ የመልካምነትህ አዝ:- አቤት የመልካምነትህ አቤት የአባትነትህ አቤት እኔን አኑረሃል አቤት እንዲህ አሳድገህ (2x) ዐይኖቹን አንስቶ አንተን የጠበቀ (3x) መች እንዲሁ ይቀራል ትጐበኘዋለህ (3x) ተሰብረህ ማትወጋ ለተደገፉብህ (3x) አቅም ትሆናለህ በእውነት ለሚጠሩህ (3x) ስለአንተ ላወራ እኔም ልናገር እድሉን አገኘሁ ከአረክላቸው ጋር በአንተ ነው ያየሁት ብሩህ ቀን ለራሴ ወደ ደካማው ሰው ስትመጣ እየሱሴ (2x) እንዴት ነው ምትወደኝ እኔን ምንም ሳልሰራልህ ለምን ምን አይነት ፍቅር ነው ያለህ እኔን የወደድክበት (2x) እኔማ (8x) እኔማ ያየሁት ኢሄን ነው እኔማ ኢየሱስ በዘመኔ እኔማ መልካምነትህን እኔማ ባወራው ከልቤ አዝ:- አቤት የመልካምነትህ አቤት የአባትነትህ አቤት እኔን አኑረሃል አቤት እንዲህ አሳድገህ (2x) ዐይኖቹን አንስቶ አንተን የጠበቀ (3x) መች እንዲሁ ይቀራል ትጐበኘዋለህ (3x) ተሰብረህ ማትወጋ ለተደገፉብህ (3x) አቅም ትሆናለህ በእውነት ለሚጠሩህ (3x) ከፊትህ ጋር ደስታ አጠገብከኝ እኔን ዘመኔ ለምልሟል ብርሃንህ በራና ሕይወቴን የገዛ የድንግዝግዝ ኑሮ ላላየው አለፈ ሁሉ ተቀይሮ (2x) እንዴት ነው ምትወደኝ እኔን ምንም ሳልሰራልህ ለምን ምን ዐይነት ፍቅር ነው ያለህ እኔን የወደድክበት (2x) እኔማ (8x) እኔማ ያየሁት ኢሄን ነው እኔማ ኢየሱስ በዘመኔ እኔማ መልኩን ልጥራው እኔማ ባወራው ከልቤ