Song Lyrics

ቸኮለብኝ ልቤ

Yidnekachew Teka
Chekolebign Libe Liyagegnih
ሌላ ነገር ታገስ ብትለኝ ጠብቃለሁ እስኪሆንልኝ ግን አባቴ ለክብርህ ነገር በህልውናህ ውሎ ለማደር አዝ:- ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ እንዴት ብዬ ኢየሱስ ልያዝህ ናፍቆቴ ነህ የሁሌ አምሮቴ አንተን ማየት ክብርህ ጉጉቴ (2x) ኢየሱስ ዓይኔ በርቶ አንዴ ልይህ ኢየሱስ ውስጤ ራበኝ እስከምነካህ ኢየሱስ እኔ አልችልም መኖር ካለዚያ ኢየሱስ በሌለበት ክብርህ ህልውናህ (2x) አዝ:- ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ እንዴት ብዬ ኢየሱስ ልያዝህ ናፍቆቴ ነህ የሁሌ አምሮቴ አንተን ማየት ክብርህ ጉጉቴ (2x) አንተን ማየት ክብርህ ጉጉቴ አባትዬ ፊትህ ጉጉቴ ኢየሱሴ ክብርህ ጉጉቴ አባትዬ ክብርህ ኢየሱሴ ኢየሱሴ የነካው ሰው ኢየሱስን በዓይኑ ያየ ሰው ኢየሱሴ የገባው ሰው ኢየሱስን በዓይኑ ያየ ሰው ለሌላ ነገር መኖር አይችልም (2x) ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም (2x) የመቅደስን ደጅ የሚጠኑ ብዙ ናቸው አንተን የሚሹ አምላክህን አሳየኝ ሚሉኝ ክብሩ የታል እስኪ አሳውቀን ወዴት ልበል የት ጋር ነህ ውዴ በእኔ ዘመን ይረፍ ትውልዴ ከእኔ ውጪ የትም አልጠቁም በእኔ ላይ ና እስኪያይህ ሁሉም (2x) ኢየሱስ ዐይኔ በርቶ አንዴ ልይህ ኢየሱስ ውስጤ ራበኝ እስከምነካህ ኢየሱስ እኔ አልችልም መኖር ካለዚያ ኢየሱስ በሌለበት ክብርህ ህልውናህ (2x) የጭንቅ ነው ስጠራህ ውዴ የውስጤን ምጥ ቃላት ሰብስቤ ቢነግርልኝ የልቤን ጩኸት የጥማቴን የርሃቤን ልክ እስከመቼ እንዲሁ በልማድ ያሰለቻል ሲደገም ትላንት ብዙ ክብር ብዙ ህልውና አዲስነት በየማለዳ (2x) ኢየሱሴ የነካው ሰው ኢየሱስን በዓይኑ ያየ ሰው ኢየሱሴ የገባው ሰው ኢየሱስን በዓይኑ ያየ ሰው ለሌላ ነገር መኖር አይችልም (2x) ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection