Song Lyrics

ማዕረጉ

Tekeste Getnet
Negestat Bikeyeru
ዝም ቢል አንደበት እጆችም ባይዘረጉ አይቀንስ ችሎታው አይቀንስ ማዕረጉ የሰማይ ቅዱሳን ደግሞም መላዕክቱ ሁሌ ይቀኙለታል ላፍታም ሳይታክቱ ካፅናፍ እስካፅናፍ ተርፏል የሚያመልከው የፍቅሬን ነው እንጂ እርሱ ምን ሊጎድለው የዳንኩ እኔ ያመለጥኩ እኔ ተፈወስኩ እኔ የሞተው ለእኔ እቀኛለሁኝ ለመድህኔ (2x) እዘምራለሁ ለመድህኔ (2x) ቢወደድ አይበዛ ቢፈቀር አይበዛ ክበር ቢባል አይበዛ ቢመሰገን አይበዛ ነፍሴን ከሞት ስለገዛ ክበር ቢባል ከቶ አይበዛ ነፍሴን ከሞት ስለገዛ ክበር ቢባል ከቶ አይበዛ አከብርሀለሁ (4x) እወድሀለሁ (4x) እንካ ተቀበለው አምልኮዬ ይኸው እንካ ተቀበለው ዝማሬየም ይኸው እንካ ተቀበለው ምስጋናዬ ይኸው እንካ ተቀበለው መጓደዴም ይኸው ዝም ቢል አንደበት እጆችም ባይዘረጉ አይቀንስ ችሎታው አይቀንስ ማዕረጉ የሰማይ ቅዱሳን ደግሞም መላዕክቱ ሁሌ ይቀኙለታል ላፍታም ሳይታክቱ ካፅናፍ እስካፅናፍ ተርፏል የሚያመልከው የፍቅሬን ነው እንጂ እሱ ምን ሊጎድለው የዳንኩ እኔ ያመለጥኩ እኔ ተፈወስኩ እኔ የሞተው ለእኔ እቀኛለሁኝ ለመድህኔ (2x) እዘምራለሁ ለመድህኔ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection