Song Lyrics

ያስታውቅብኛል

ምነው ይበጃል ውይ ዝም ማለት ምነው ይሄ ሁሉ ተደርጐለት ምነው ሌላ ቃላት በተገኘ ምነው ልቤ ቢልህ እንደተመኘ ያስታውቅብኛል የተገለጠ ነው የሱን መልካምነት አልችልም ልደብቀው አቅም እየሆነ ብርታት እየሆነ ሞገስ እየሆነ እዚህ እንዳደረሰኝ ምልክት ለሚሻ እኔን ይመልከተኝ ይሄው ምሥጋናዬ/፪ ፍቅሬን የምገልጥበት አንድ ያለኝ ስጦታዬ ይሄው ዝማሬዬ/፪ መውደዴን ማወራበት አንድ ያለኝ ስጦታዬ ቸርነትህ ብዙ ብዙ በጐነትህ ብዙ ብዙ ስትረዳ ብዙ ብዙ / ይወራ ይነገር ለኔማ ያረከው ነገር /፪ 1)ምን መላ አለው እየተባለ ከሰው ተራ የተገለለ ቸርነትን ከአንተ አግኝቶ ያካብርሀል በፊትህ ቆሞ ቸርነትህን ላውራው ላውራው ሰው የሆንኩት በአንተ ነው በአንተ ነው በጉነትህን ላውራው ላውራው ሰው የሆንኩት በአንተ ነው በአንተ ነው / ይወራ ይነገር ለኔማ ያረከው ነገር/፪ ያስታውቅብኛል የተገለጠ ነው የሱን መልካምነት አልችልም ልደብቀው አቅም እየሆነ ብርታት እየሆነ ሞገስ እየሆነ እዚህ እንዳደረሰኝ ምልክት ለሚሻ እኔን ይመልከተኝ ይሄው ምሥጋናዬ/፪ ፍቅሬን የምገልጥበት አንድ ያለኝ ስጦታዬ ይሄው ዝማሬዬ/፪ መውደዴን ማወራበት አንድ ያለኝ ስጦታዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection