Song Lyrics

የሁሌ

ፍቅር የጎደለበት ባግባቡ እንኳን ያልኖረ አይዞ ባይ ወገን የሌለው ብቸኛ የነበረ ያለበት ድረስ መተህ ወድሃለው ስትለው ልቡን ከማፍሰስ በቀር ምንስ ሌላ አማራጭ አለው መመክያ (X3) አንተ ነህ ጌታዬ (X2) ላፍታ ሳትለየኝ በድካም ሆነ በብርታት ስንት ግዜ ረዳኀኝ ባሳለፍኳቸው አመታት ልቤን ኩራት አለው ዘንድሮም ተመካብህ የማትለዋወጥ ህይወት ዋስትና ነህ የሁሌ ነህ የሁሌ አምላኬ ነህ የሁሌ አፍቃሪ ወረት የለብህ ውዴ ልበልህ እንዳመሌ ማይዘነጋ ነው አይጠፋም ከሃሳቤ ሁሌ ድቅን ይልብኛል ፍቅርህ ታትሟል በልበ ብዙ ወጀብ አልፎ ትኩሳት እንዳው አይበርድም ዛሬም አንተኑ ይለኛል አለውጥህም በማንም የሁሌ ነህ የሁሌ ማይዘነጋ ነው አይጠፋም ከሃሳቤ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection