Song Lyrics

ወትሮም

እኔ እንደው ልማዴ ነው ሳይነጋ መዘመር እኔ እንደው ልማድ አለኝ ችግር ፊት መዘመር ስላንተ ሲወራ ደስ ደስ ይለኝ ጀመር ሁሉ ደህና ነው ስል ደህና ሆኖ ቀረ አስፈሪው ተራራ ሆነ እንዳልነበረ ድሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ ወትሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ ልበልህ ጌታዬ /3× ልበልህ ንጉሴ /3× ድሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ ወትሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ የዕለቱን መስዋዕት ከእኔ የሚሻው ላሳርግለት ያውድ መዓዛው አያፍርም ፊቴ እርሱ ጋ ደርሶ ይለውጠዋል ሁሉን አድሶ ጥያቄ ኖሮ ያልተመለሰ መዘመር አልተው ፍቅሬም አልቀነሰ ማጠኛውን ስጡኝ የተራዬን ልበል እኔ ጋር ደርሶ አምልኮ አይጓደል ድሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ ወትሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ ላስተዋለውማ ተፈጥሮም ያወራል ሊነጋጋ ሲቀርብ እጅግ ይጨልማል ምልክት ነበር ድቅድቅ ማለቱ የመጎብኛዬ ደረሰ ሰዓቱ ድሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ ወትሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ ልበልህ ጌታዬ /3× ልበልህ ንጉሴ /3× ድሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ ወትሮም የበላይ ነህ ክብር ነው መገኛህ እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection