Song Lyrics

አይቀርም

ሞላ አልሞላ የምለው ጉዳይ ቢኖረኝም አለማመስገን እኔ ከቶ አይሆንልኝም እኔ እንደ ልማዴ መዘመር ስጀምር ባስጨነቀኝ ላይ ዛሬም ይገለጣል ክብር ጉዳይ አለኝ የማዋይህ ለልቤ ንጉስ ማንጎራጉርልህ ነገር አለኝ የማዋይህ ለልቤ ንጉስ ማንጎራጉርልህ ምስጋና የሚሠዋ ማዳንህን እንዲያይ በርግጥ ለሚወዱህ መላ አለህ ከሰማይ ደግሞ እድሉ ደርሶኝ ደግሞ ሳይገባኝ ደግሞ በራሱ ፀጋ ደግሞ ዘምር ካለኝ ደግሞ እንዲህ እንድያ የሚል ደግሞ ቆስቋሽ ለምኔ ደግሞ የተሰራልኝ ደግሞ በቂ ነው ለኔ ያለው አይቀርም አምናለሁ ዝማሬ ካፌ አይታጣ የካሳ ጊዜ ይሆናል ቀን ቆጥሮ ለኔ ሲመጣ እግዚአብሔር ነው ጉልበቴ መዝሙር በለሊት የሰጠኝ ቃል ገብቶልኛል አውቃለሁ ላይጥለኝ ደግሞ ላይተወኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection