Song Lyrics

በማደሪያው ላይ

Tekeste Getnet
Negestat Bikeyeru
አይጓደልም ልማዴ እሰግዳለሁኝ ለውዴ ሆነ አልሆነ ነገሩ አባቴ አለ በመንበሩ አይቋረጥም ልማዴ እሰግዳለሁኝ ለውዴ ሞላ አልሞላ ነገሩ እግዚአብሔር አለ በመንበሩ አዝ፦ በማደሪያው ላይ በዙፋኑ ላይ በመንበሩ ላይ በከፍታው ላይ አለ የሚሰማ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ አለ የሚፈውስ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ መጣሁ ላመልከው መጣሁ ላደናንቀው መጣሁ ተመስገን ልለው መጣሁ ፍቅሬን ልነግረው ሌላማ መሻት የለኝም ኢየሱስ ይክበርልኝ ሌላማ አምሮት የለኝም ኢየሱስ ይክበርልኝ አይጓደልም ልማዴ እሰግዳለሁኝ ለውዴ ሆነ አልሆነ ነገሩ አባቴ አለ በመንበሩ አይቋረጥም ልማዴ እሰግዳለሁኝ ለውዴ ሞላ አልሞላ ነገሩ እግዚአብሔር አለ በመንበሩ አዝ፦ በማደሪያው ላይ በዙፋኑ ላይ በመንበሩ ላይ በከፍታው ላይ አለ የሚሰማ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ አለ የሚፈውስ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ ክበር ልበልህ ንገስ ልበልህ ያለኝ ይሄ ነው ይሄ ነው አምልኮን ላንተ አበዛለሁ ያለኝ ይሄ ነው ይሄ ነው ውዳሴን ላንተ አበዛለሁ ለአስራ ስምንት አመታት መሬት መሬቱን እያየች አቀርቅራ ምትራመድ ጎባጣ ሴት የነበረች በቤተመቅደስ ተገኝታ ልዑልን ስታወድሰው የብዙ ዓመት መከራዋን ከላይዋ አንከባለለው አዝ፦ በማደሪያው ላይ በዙፋኑ ላይ በመንበሩ ላይ በከፍታው ላይ አለ የሚሰማ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ አለ የሚፈውስ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection