Song Lyrics

ያድናል

Tekeste Getnet
Negestat Bikeyeru
ጌታ ነው ቢጎድልም ቢሞላ በሕይወቴ የለም ከእርሱ ሌላ ችግሩ ከቦ ቢያስጨንቀኝ ከርስቴ ማን ሊነቀንቀኝ እኔ አለሁ (2x) አልነሳም ከመሰዊያው (2x) ጌታ ነው ቢጎድልም ቢሞላ በህይወቴ የለም ከሱ ሌላ ችግሩ ከቦ ቢያስጨንቀኝ ከርስቴ ማን ሊነቀንቀኝ እኔ አለሁ (2x) አልነሳም ከመሰዊያው (2x) እየተፀለየ እየተዘመረ ከቀደመው ይልቅ ችግሩ ጨመረ ሰባት እጥፍ ቢሆን ጨምሮ ጨምሮ እግዚአብሔር ያድናል ችግርን ሰባባሮ እየተፀለየ እየተዘመረ ከቀደመው ይልቅ እሳቱ ጨመረ ሰባት እጥፍ ቢነድ ጨምሮ ጨምሮ እግዚአብሔር ያድናል የእሳትን ኃይል ሰብሮ ያድናል ዛሬም/እኮ ያድናል ለጌታ ምን ይሳነዋል ሕያው ነው አልተለወጠም ያድናል ለዘላለም (2x) የሰጠ እርሱ አይደለም ወይ ቢነሳ ከልካይስ አለው ወይ አትበይ እንደሰነፎች ከሁሉ ጌታ ነው የሚመች እኔ አለሁ (2x) አልነሳም ከመሰዊያው (2x) እንዲህ ነው አይባል የጌታ አሰራሩ (2x) ፈፅሞ አይታማም ግሩም ነው በምክሩ (2x) ቢዘገይም እንኳን በጊዜው ይደርሳል (2x) ካለቀሰ ሁሉ እንባ ይታበሳል (2x) ያድናል ዛሬም ያድናል ለጌታ ምን ይሳነዋል ሕያው ነው አልተለወጠም ያድናል ለዘላለም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection