Song Lyrics

ድረስለት

Tekeste Getnet
Negestat Bikeyeru
እልፍ ጥያቄ እልፍም ችግር ታቅፎ የኖረ ሳያንገራግር ችግሩን ቻል አድርጎ ጌታ ይበልጣል ብሎ ሲያመልክ ባደባባይ ይሰማ በአንተ ዘንድ ይታይ አዝ፦ ይረዳል ይበል ተረድቶ ያግዛል ይበል ታግዞ ድረስለት ለእንዲህ ዓይነቱ ሰው (2x) ባዶውን እንዲሁ አትመልሰው (2x) ሲማፀን በቆመበት ስፍራ (2x) አለሁ በለው ስምህን ሲጠራ (2x) አዝ፦ ይረዳል ይበል ተረድቶ ያግዛል ይበል ታግዞ ከወገኖቹ ከሀገር እርቆ በባእድ ምድር ሚኖር ተሳቆ ያሰበው ባይሞላለት ሲያለቅስ በያለበት ራራ ስማው አቤቱ አለሁ በል ለእንዲህ ዓይነቱ አዝ፦ ይረዳል ይበል ተረድቶ ያግዛል ይበል ታግዞ ድረስለት ለእንዲህ አይነቱ ሰው (2x) ባዶውን እንዲሁ አትመልሰው (2x) ሲማፀን በቆመበት ስፍራ (2x) አለሁ በለው ስምህን ሲጠራ (2x) አዝ፦ ይረዳል ይበል ተረድቶ ያግዛል ይበል ታግዞ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection